Get Mystery Box with random crypto!

’የረዳነው ተርፎን ሳይሆን ህይወትን ለማዳን ካለን በማካፈል ነው፡፡” አፋሮች! የአፋር ክልላዊ መን | DW Amharic

’የረዳነው ተርፎን ሳይሆን ህይወትን ለማዳን ካለን በማካፈል ነው፡፡” አፋሮች!
የአፋር ክልላዊ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ እርዳታ ፈላጊዎች የሚሆን የእለት እርዳታ ማድረጉን አስታወቀ:: ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ በክልሉ የተከሰተውን ቀውስ እንዲታደጉ የክልሉ መንግስት ጥሪ አድርጓል፡፡
የአፋር ክልል መንግስት የአደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት ክልሉ ተርፎት ሳይሆን ካለው በማካፈል በትግራይ ክልል በችግር ለተጋለጡ ወገኖች የእለት እርዳታ የሚሆን 9 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 2ሺህ 700 ኩንታል ምግብ የእለት እርዳታ አቅርቧል፡፡
በአጠቃላይ ክልሉ ደረገው ድጋፍ 1500 ኩንታል ሩዝ፣ 900 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 200 ኩንታል ጨውና ሌሎችም ምግብ ነክ እርዳታዎች ይገኙበታል፡፡
አቶ መሐመድ እንዳሉት በክልላቸው ባለፉት የክረምት ወራት በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተፈጥረው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተፈናቅለው እንደነበር አስታውሰው፣ ዛሬ ያደረጉት እርዳታ ተርፏቸው ያደረጉት ሳይሆን ወገንን ለማዳን ካላቸው በማካፈል የተደረገ እርዳታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድጋፍ በማድረግ በትግራይ ክልል ያንዣበበውን ሰብአዊ ቀውስ መታደግ እንደሚገባቸው ጠይቀዋል፡፡
በትግራይ ክልል አንዳንዶቹ 4 .5 ሚሊዮን ህዝብ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ መጋለጡን ሲያመለክቱ የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የተባለው ቁጥር በመረጃ ያልተደገፈ መሆኑና ትክክለኛ በክልሉ ያለው የተረጂ ቁጥር ከ2.5 ሚሊዮን እንደማይበልጥ በተደጋጋሚ አመልክቷል፡፡ የባህርዳሩ ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን እንደዘገበው ከትግራይ ክልል ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ጥረት ባለስልጣናቱ ስልክ ማንሳት ባለመቻላቸው አልተሳካም፡፡