🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ ዛሬ ሌሊት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይ | DW Amharic

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ ዛሬ ሌሊት በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳዋ ፖሊስ አስታወቀ። ፖሊስ እንዳለው በርካታ ሰዎችን ከሌላ ጭነት ጋር ደርቦ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ በወረዳዋ ሀርአምባ ቀበሌ ልዩ ስሙ ልጄን አደራ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በመገልበጡ የስድስት ሰዎች ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 30 ያህል ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሷል። የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘገባ እንዳመለከተው ተሽከርካሪው በጫነው 39 ኩንታል ጤፍ ላይ 87 ሰዎችን ደርቦ ጭኖ ይጓዝ ነበር።የአደጋው ምክንያትም ዳገት ላይ ደርሶ ወደ ኋላ በመንሸራተት ወንዝ ውስጥ በመግባቱ መሆኑን የወረዳዋ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጂን ዘነበ ወልዴ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በአደጋው የተጎዱት በጎረቤላ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የጤና ጣቢያው ኃላፊ አቶ ተዋበ አይችሉህም ገልጸዋል።