Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ። « | DW Amharic

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በርካታ ሴቶች የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባቸው መንግስት ማረጋገጫ ሰጠ። «በክልሉ በሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት መፈጸሙን በስፍራው ካለው ግብረኃይላችን መረጃ አግኝንተናል» ሲሉ የሴቶች ሚንስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ ትናንት ሐሙስ ምሽት በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። የፌዴራሉ መንግስት « ህግ የማስከበር ዘመቻ» ባለው እና ሕወኃት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በሴቶች ላይ በተከታታይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሲደርስባቸው እንደነበር የአይን ምስክሮች ፣ የህክምና ባለሞያዎች እና የረዲኤት ሰራተኞች ሲያስታውቁ ቆይተዋል። በመንግስት በኩል ለደረሰው ጥቃት እውቅና ሲሰጥ የሚንስትር ፊልሰን አብዱላሂ የመጀመርያው ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን እንዳስታወቀው በትግራይ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በክልሉ መዲና የመቀሌ ከተማ በሁለት ወር ውስጥ የተፈጸመ እንደነበር ገልጿል። ከፊሎቹ ተጠቂዎች ጥቃቱን ያደሩሳበቸው የፌዴራል መንግስቱ ወታደሮች እና አጋሮቻቸው እንደሆኑ ቢገልጹም የጥቃት አድራሾችን ብዛት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አለመቻሉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እንደሚለው የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሪፖርት ያልተደረገባቸው አካባቢዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክቷል።መንግስት ጾታዊ ጥቃትን እንደማይታገስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።
ፎቶ/የኢትዮጵያ ሴቶች ሚንስትር