Get Mystery Box with random crypto!

አጣሪ ጉባኤው ባለፉት 5 ዓመታት 14 ጉዳዮችን ብቻ ተመለክቷል! ህብረተሰቡ የህገመንግስት ትርጉም | DW Amharic

አጣሪ ጉባኤው ባለፉት 5 ዓመታት 14 ጉዳዮችን ብቻ ተመለክቷል!
ህብረተሰቡ የህገመንግስት ትርጉም የሚስፈልጋቸውን ጥያቄዎች ባግባቡ መገንዘብ ባለመቻሉ ባለፉት 5 ዓመታት የቀረቡ አቤቱታዎች በጣም ዝቅተኛ መሆናቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
የፍርድ ቤቱ ፕረዚደንትና የአማራ ክልል ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ አቶ አብዬ ካሳሁን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከ2008 ዓ ም ጀምሮ 14 ብቻ የህገ መንግስት ትርጉም አቤቱታዎች ቀርበዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 4ቱ የህገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው አቤቱታዎች ሆነው በመገኘታቸው በውሳኔ ሀሳብ በማስደገፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ለአማራ ክልል ህገመንግስት ተርጓሚ ኮሚሽን ተልከው የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል እንዲፀኑ መደረጉንም አቶ አብዬ ተናግረዋል፡፡
10ሩ ደግሞ እንደማያስፈልጋቸው የውሳኔ ሀሳብ እንደቀረበባቸውም አስረድተዋል፡፡ የአቤቱታዎቹ ቁጥር አናሳነት ችግር አለመኖሩን የሚያሳዩ እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕረዚደንቱ፣ በየደረጃው የህገመንግስት ትርጉም የሚሹ ኢ ህገመንግስታዊ ህጎች፣ የተዛቡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና የፍርድ ቤት ዳኝነቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ መብቱን ወደ ህገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አቤት ማለት አለባቸው ሲሉ አመልክተዋል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ ካለው የህዝብ ቁጥር አኳያ የህገመንግስት ትርጉም አቤቱታዎች በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘታቸው ህብረተሰቡ ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንደሌለው ማሳያ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዬ፣ የህግ አዋቂዎች፣ ብዙሀን መገናኛና የህግ ተቋማት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ አሳስበዋል፡፡
አማራ ክልል 11 አባላት ያሉት የህገ መንግስት አጣሪ ጉበኤ አሉት፡፡