Get Mystery Box with random crypto!

ናይጄሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ልዌላ የዓለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር መሆናቸው ተረጋገጠ። ኦኮንጆ ልዌ | DW Amharic

ናይጄሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ልዌላ የዓለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር መሆናቸው ተረጋገጠ። ኦኮንጆ ልዌላ 164 አባል ሃገራትን ያቀፈውን ዓለም አቀፉን ተቋም በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ሹመታቸው ዛሬ ሲረጋገጥ ዓለም አቀፍ የንግድ አለመግባባቶችን መፍታት ተቀዳሚ ተግባራቸው እንደሚሆን ይጠበቃል። አዲሷ የዓለም የንግድ ድርጅት ተሿሚ ሹመታቸው የተረጋገጠው አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታን ካገኘ በኋላ ነው ተብሏል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ቀርቦላቸው የነበረውን የኦኮንጆ ልዌላን ሹመት ወደ ጎን ገፍተውት ነበር። የባይደን ርምጃ ቀደም ሲል ዶናልድ ትራምፕ ዓለም አቀፍ የንግድ ትብብሮችን ለአደጋ አጋልጦ እንደነበር የሚነገርለት እና «አሜሪካ ትቅደም» አቀራረባቸውን በማስቀረት አንድ እርምጃ ወደ ፊት ያራመደ ነው እየተባለ ነው። የናይጄሪያ የገንዘብ ሚንስትር የነበሩት ኦኮንጆ ልዌላ ከ25 ዓመታት በላይ ያገለገሉበት እና እስከ ሁለተኛው የሥልጣን እርከን ያደረሳቸው የዓለም ባንክ አገልግሎታቸው እና ልምዳቸው ለአዲሱ የሥራ ኃላፊነት እንዳሳጫቸው የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ ያሳያል። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ፍትሃዊ ያልሆነ አያያዝ ይከተላል በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱ ቆይተዋል።