Get Mystery Box with random crypto!

የእስራኤሏ የቴልአቪቭ ከተማ ነዋሪቿ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት ነጻ የምግብ ዕደላ | DW Amharic

የእስራኤሏ የቴልአቪቭ ከተማ ነዋሪቿ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት ነጻ የምግብ ዕደላ መጀመሯን አስታወቀች። ከተማዋ የማበረታቻ እርምጃውን ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው አጎራባች የሆነችው የበናይ ብራክ ከተማ ተግባራዊ ማደግ ከጀመረች በኋላ መሆኑ ተነግሯል። በከተማዋ በተለይ የተሕዋሲው ስርጭት በርትቶ በታየባቸው እና ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኝነቱ ባልታየባቸው ሁለት አካባቢዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ነጻ የምግብ አቅርቦት እንደ ማበረታቻ ቀርቦላቸዋል ነው የተባለው። «ይህን በማድረግ የተሕዋሲውን ስርጭት በመቆጣጠር የትምሕርት፣ የንግድ እና የባህል ተቋማት ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ እና መደበኛው እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን በፍጥነት እንዲጀመር የተቻለንን እናደርጋለን» ሲሉ ከንቲባው ሮን ሁልዳይ ተናግረዋል። እስራኤል ከ9,3 ሚሊዮን ዜጎቿ አንድ አራተኛው የሚሆኑት ተከታትለው የሚሰጡትን ሁለቱን ክትባቶች መከተባቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ ዘግቧል።