Get Mystery Box with random crypto!

ካለፉት ሳምንታት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን እና | DW Amharic

ካለፉት ሳምንታት ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን እና የለውጡን አመራር የሚደግፉ ሰልፎች በመካሄድ ላይ ናቸው። በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የጀመረው ይኸው የድጋፍ ሰልፍ በምዕራብ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያም የተደረገ ሲሆን በዛሬውም ዕለት እንደ ኮምቦልቻ ፣ ደሴ፣ ከሚሴ እና ባቲ ባሉ ከተሞች በመካሄድ ላይ ነው።
የምርጫ ቅስቀሳ ከትናንት የካቲት 8 ቀን 2013 አንስቶ በይፋ እንደሚጀመር የተገለጸ ቢሆን እስካሁን የተፎካካሪ ፓርቲዎች መሰል ሰልፍ መካሄዱ አልተሰማም። ተቺዎች ሰልፍ የሚፈቀደው ለብልፅግና ፓርቲ ወይም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋፊዎች ብቻ ነው ሲሉ ይደመጣል። ወቅቱ የኮቪድ 19 ተሐዋሲ እንዳይስፋፋ የሚሰጋበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ምን ያህል ታስበዋል ማለት ይቻላል?https://www.facebook.com/dw.amharic/photos/a.507141705985597/4167865066579891