Get Mystery Box with random crypto!

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረዉን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር ማቋረጥዋ ከህዳሴ ግን | DW Amharic

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረዉን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር ማቋረጥዋ ከህዳሴ ግንባታ ጋር የነበረዉን የምክንያት ግንኙነት ሰረዘች። የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ህዳሴ ግድብ ያቀረቡትን የኢትዮጵያ መንግሥት አለዉ ባሉት ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረዉን ከ 270 ሚሊዮን ዶላር በላይ አቋርጠዉ ነበር። አዲሱ የጆ ባይደን አስተዳደር አሁን እንዳስታወቀዉ ግን ብድር ማቋረጡ ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ምክንያት መሆኑን ሰርዞአል። ይሁንና የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚ/ር እንዳለዉ የተቋረጠዉ ብድር አሁን ለኢትዮጵያ ይሰጣል ማለት አይደለም። ሚኒስትር መስርያ ቤቶ አክሎ እንዳስታወቀዉ ብድሩ የሚሰጠዉ አሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ሁኔታ ከመሻሻሉ ጋር በተያያዘ ነዉ። የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ሁኔታ ያለዉን በቀጥታ አልጠቀሰም ። ጋዜጠኞች ግን ትግራይ ዉስጥ የሚታየዉን ግጭት ሳይሆን እንዳልቀረ ገምተዋል። ሌላዉ የዩናይትድ ስቴትስ ሰብዓዊ ርዳታ በዚህ ብድር መያዝ ምክንያት እንደማይነካ መስርያቤቱ አስታዉቋል። ስለጉዳዩ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት መግለፁንም አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቦአል። ዶናልድ ትራምፕ ስለህዳሴ ግድብ ያቀረቡትን ሃሳብ ኢትዮጵያ ባለመቀበልዋ ምክንያት አሜሪካ የምትሰጠዉን ብድር በማቋረጣቸዉ በርካታ ኢትዮጵያዉያንን አስቆጥቶ ነበር።