Get Mystery Box with random crypto!

የረቡዕ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ፣ መንግሥትን | DW Amharic

የረቡዕ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ፣ መንግሥትን ለመገልበጥ በማሴርና በአሸባሪነት የጠረጠራቸው ታዋቂው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው አሁን ከሚገኙበት ከዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አስታወቁ። በፈቃዳቸው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የቀረበባቸውን ውንጀላ በፍርድ ቤት ለመከራከር ዝግጁ መሆናቸውን በተለይ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ የተናገሩት አቶ ልደቱ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ጅዲ ሳዑዲ አረብያ ውስጥ የተኩስ አቁምና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያካሂዱት ንግግር በቀጠለበት በዛሬ እለት በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል በዋና ከተማይቱ ኻርቱም የሚካሄደው ውጊያ መቀጠሉን ነዋሪዎች ተናገሩ። ለንግግሩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቶች እንዳሉት፣ ሁለቱ ወገኖች ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በጅዳ በሚያካሂዱት ንግግር የተጨበጠ ውጤት ላይ አልደረሱም።

ቱኒዝያ በሚገኝ አንድ ደሴት ውስጥ ባለ ሙክራብ አቅራቢያ ትናንት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ወደ አምስት ከፍ ማለቱን የሆስፒታል ምንጮች አስታወቁ። በአንድ የቱኒዝያ ብሔራዊ ዘብ አባል፣ የሀገሪቱ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የጀርባ አጥንት በሆነችው በጀርባ ደሴት ስለተፈጸመው የተኩስ ጥቃት መንስኤ የቱኒዝያ ባለሥልጣናት ያሉት ነገር የለም።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4RARg?maca=amh-RED-Telegram-dwcom