Get Mystery Box with random crypto!

አርዕስተ ዜና -በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙት የአፋር ክልል የመሠረተ ልማት አዉታሮች እስካሁ | DW Amharic

አርዕስተ ዜና

-በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙት የአፋር ክልል የመሠረተ ልማት አዉታሮች እስካሁን አለመጠገናቸዉን ነዋሪዎች አስታወቁ።የእረብቲና የአብአላ ወረዳዎች ነዋሪዎች እንዳሉት የስልክ፣የኢንተርኔት፣የመብራት አገልግሎት፣ የትምሕርትና የጤና ተቋማት ባለመጠገናቸዉ ነዋሪዉ እየተቸገረ ነዉ።የተቀበሩ ፈንጂዎች ደግሞ ሕፃናትን እየገደሉ ነዉ።

-የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ተኩስ እንዲያቆሙ ለማግባባት ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የተያዘዉ ሽምግልና የተስፋ ጭላንጭል ማሳየቱን ሸምጋዮች አስታወቁ።የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከሚሽነር ተፋላሚዎችን አወገዙ።ዉጊያዉ እንደቀጠለ ነዉ።

-ጦርነት፣ግጭትና የተፈጥሮ መቅሰፍት ከቤት ንብረቱ ያፈናቀለዉ ሕዝብ ቁጥር ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ማሻቀቡን አጥኚዎች አስታወቁ።የተፈናቃዩ ቁጥር ከ71 ሚሊዮን በልጧል።በርካታ ሕዝብ ከተፈናቀሉባቸዉ 10 ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
https://p.dw.com/p/4REN2?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot