Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተነገረ ጂዳ ሳዑዲ አረብያ | DW Amharic

የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት በቅርቡ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተነገረ
ጂዳ ሳዑዲ አረብያ ውስጥ የሚነጋገሩት የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸው ተሰማ ። የሱዳን ጦር ሠራዊትና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል የተኩስ አቁምና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ስምምነት ላይ ለመድረስ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ እየተነጋገሩ ቢሆንም እስከ ትናንት ድረስ የተጨበጠ ውጤት ላይ አለመድረሳቸው ነበር የተሰማው።ሆኖም አንድ ሸምጋይን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሁለቱ ወገኖች ድርድር ውጤት እያሳየ ነው፤ በቅርቡም የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሌላ ምንጭም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረባቸውን ተናግረዋል።ንግግሩ ትናንት ለሊትም ቀጥሎ እንደነበርም ገልጸዋል።