Get Mystery Box with random crypto!

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ የተለ | DW Amharic

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በሎስ አንጀለስ ካሊፎርንያ እንደሚወያዩ የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መስሪያ ቤቱ በድረ ገጹ እንደጻፈው እስከ መጪው አርብ በሎስ አንጀለስ የተለያዩ የንግግር ቀጠሮች ያሏቸው አምባሳደር ሀመር ከኢትዮጵያውያን ጋር ከሚወያዩባቸው ጉዳዮች ውስጥ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ያስቆመው ስምምነት አተገባበር ይገኝበታል። ሀመር ከአማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌና የትግራይ ማኅበረሰብ ቡድኖች ተወካዮች ፣እንዲሁም በአጠቃላይ ከአሜሪካዊ ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ጋር ይወያያሉ ሲል የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።