🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሕገመንግሥትን የተመለከተ ጥናት ያካሄደው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ተቋም በግኝቱ ኅብረተሰቡ አንድ ላይ ከመ | DW Amharic

ሕገመንግሥትን የተመለከተ ጥናት ያካሄደው የኢትዮጵያ ፖሊሲ ተቋም በግኝቱ ኅብረተሰቡ አንድ ላይ ከመኖር የተለየ ሃሳብ እንደሌለው መረዳቱን አመለከተ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የጥናቱ አስተባባሪ ዶክተር ጥላሁን ተፈራ እንደተናገሩት፤ ትኩረት የተደረገባቸው የተመረጡት አንቀጾች አነጋጋሪዎች እና አነታራኪዎች ቢሆኑም በዚህ ጥናት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚፈልጉት አብሮነትን መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል። የፌደራላዊት ሪፑብሊክ ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን በተመለከተ ሦስት እሳቤዎች እንደሚታዩ ያመለከቱት ዶክተር ጥላሁን ፤ «አንዱ ይኽ ሕገ መንግሥት በምንም መልኩ መነካት የለበትም እንደውም ተጠናክሮ በደንብ ወደ መሬት መውረድ አለበት ሲል፤ ሌላኛው ጽንፍ ሕገ መንግሥቱ የተጻፈበትን ቀለም እንኳ ያህል ዋጋ የለውም ተቀዶ መጣል አለበት በሚል ያጣጥላል፤ ሦስተኛው ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ነገሮች አሉት እነሱን ማስቀጠል፤ የሚሻሻሉ ካሉ ደግሞ እነሱን እያሻሻሉ መቀጠል እንጂ ከዜሮ መጀመር አስፈላጊ አይደለም» የሚል መሆኑን በመዘርዘር በዚህ መነሻነት ጥናቱ መካሄዱን ተናግረዋል። በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታዩት ብሔር ተኮር ግጭቶች በዋነኛነት ሕገ መንግሥቱን ተጠያቂ የማድረግ አካሄድ ይታያል ያሉት የጥናቱ አስተባባሪ መንግሥትን እንደሚያማክር አንደ አንድ መንግሥታዊ ተቋም ልኂቃኑ እንደሚሉት ሕገ መንግሥቱ የችግሩ ሁሉ ምንጭ ነው ወይ የሚለውን ለመመልከት የኢትዮጵያ የፖሊሲ ተቋም ወደ ጥናቱ መግባቱንም አንስተዋል። ...