🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

...በዚህ መነሻነትም ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ከመግቢያው አንስቶ አንቀጽ 8 እንዲሁም አንቀጽ 39ኝ ጨ | DW Amharic

...በዚህ መነሻነትም ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ከመግቢያው አንስቶ አንቀጽ 8 እንዲሁም አንቀጽ 39ኝ ጨምሮ አነጋጋሪ ነጥቦች የሚባሉት ላይ በማተማኮር ጥናቱ መደረጉንም ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። «በአንዳንድ ምሁራን፤ በፖለቲካ ልኂቃን እንዲሁም የማኅበረሰብ አንቂ በሚባሉት በኩል ሕገመንግሥቱን የግጭቶች ሁሉ መነሻ አንድርጎ የመመልከት አዝማሚያ አለ» ያሉት ዶክተር ጥላሁን፤ «ጥናቱ ያሳየው ግን በዚህ ሃሳብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ስምምነት እንደሌለ ነው» ብለዋል። ጥናቱ የተደረገበት ዋና አላማም መንግሥት ተነስቶ ሕገ መንግሥቱን እቀይራለሁ በሚል ሌላ እርምጃ ውስጥ እንዲገባ ሳይሆን ሕገ መንግሥቱን በሚመለከት በቀጣይ ለሚደረግ ሀገራዊ ውይይትም ሆነ ክርክር ግብአት እንዲሆን ታስቦ መሆኑንም ነው አጽንኦት የሰጡት። በጥናቱ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት ምክረ ሃሳብም «መንግሥት ሕገ መንግሥቱ ስለመቀየር ቀነ ገደብ ሁሉ ማስቀመጥ እንደሌለበት» ማሳሰባቸውንም የጥናቱ አስተባባሪ ዶክተር ጥላሁን ተፈራ አክለው ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አመልክተዋል። ጥናቱ ሁለት ዓመታትን የወሰደ ሲሆን ከትግራይ ክልል በቀር በሌሎቹ ክልሎች ላይ መደረጉ ተገልጿል።