Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን መንግሥት ተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዋና ከተማ ኻርቱም ውስጥ 22 ሆስፒታሎችን ይዘዋል | DW Amharic

የሱዳን መንግሥት ተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዋና ከተማ ኻርቱም ውስጥ 22 ሆስፒታሎችን ይዘዋል ሲል ከሰሰ። ከትናንት በስተያ በተባባሰው ውጊያ የህክምና ተቋማቱ ከመመታታቸው በተጨማሪ መዘረፋቸው ነው የተገለጸው። የአማጺው ታጣቂዎች ሰብዓዊ መብቶችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ እና የሱዳንን መርሆና ባህሎች ሁሉ እየጣሱ ነው በማለት የሱዳን ጦር ኃይል በይፋዊ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ገጾቹ ላይ ባወጣው መረጃ ወቅሷል። ተቀናቃኞቹ ኃይላት ሰላማዊ ዜጎችና የሲቪክ ተቋማትን ከጥቃት ለመከላከል እንዲሁም ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ለማመቻቸት ባለፈው ሳምንት ተፈራርመው ነበር። ሆኖም ግጭቱ እና ውጊያው በኻርቱም እና ባህር እንዲሁም ኦምዱርማን ከተሞች ተባብሶ መቀጠሉ እየተነገረ ነው።