🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት | DW Amharic

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ የሰላም ሂደቱን ይጎዳል አለ። ህወሓት በበኩሉ የምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ዳግም እንዲያጤን ጠይቋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ህወሓት ትናንት ባወጣው በዚሁ መግለጫው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት፣ ሕጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስለት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡን በማመልከት፣ ቦርዱ ግን «ሕጋዊ ሰውነት የመሰረዝ ውሳኔ እንዲያነሳ ያቀረብንለት ጥያቄ የሰላም ስምምነቱ አላማ የሆኑ ሐሳቦችን በሚጻረር ሁኔታ ምላሽ ሰጥቷል» ሲልት ወቅሷል። ህወሓት የቦርዱን ውሳኔ «የሰላም ስምምነቱን የማይቀበል፣ የሰላም ስምምነቱን አተገባበር ባለቤት አልባ የሚያደርግ፣ በቀጣይም ለሰላሙ እንቅፋት የሚፈጥር» በማለትም ተችቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለግዜው ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት እንደማይችል ገልጿል። በዕለቱ የዜና መጽሔት ዝርዝር ዘገባ ተካቷል፤ ጠብቁን። ዶቼ ቬለን ተከታተሉ።