Get Mystery Box with random crypto!

የሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ ርዕሶቹ • የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮ | DW Amharic

የሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• የፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የፌዴሬሽኑ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ወሰነ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በቅርቡ በተከናወነው ሕዝበ ውሳኔ መሰረት የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች የተካተቱበት «የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል ስያሜ እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

• በአማራ ክልል የሸዋሮቢት ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ኃላፊ የነበሩት አቶ አብዱ ሁሴን ትናንት ማክሰኞ በደረሰባቸው ጥቃት ተገደሉ ። ከትናንት በስትያ ማክሰኞ በተመሳሳይ ምስራቅ ጎጃም የደጀን ወረዳ ሁለት የፖሊስ ኃላፊዎች ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል።

• ግጭት በተንሳራፋበት የሱዳኗ ዳርፉር ግዛት የከፋ ሰብአዊ ቀውስ እንይከተል ማስጋቱን ኢንተርናሽናል ሪስክ ኮሚቴ አሳሰበ። ዓለማቀፉ የግብረሰናይ ድርጅት እንዳለው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ36 ሺ በላይ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገር ቻድ ተሰደዋል።

• እስራኤል በኃይል በያዘችው የዮርዳኖስ ምዕራባዊ ዳርቻ ጄኒን ከተማ በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ግዙፍ ነበር የተባለለትን ወታደራዊ ዘመቻዋን ማጠናቀቋን ዐስታወቀች። በሁለቱ ቀናት የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ የተገደሉባቸውን 12 ሰዎች ለመቅበር በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን በጄኒን ከተማ ተሰባስበዋል።

• ሩስያ የጥቁር ባህር የእህል ዝውውር ስምምነት እንዲቀጥል የሀገሪቱ የግብርና ባንክ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ዝውውር ስረዓት ወይም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ SWIFT የክፍያ ስረዓት መመለስን በቅድመ ሁኔታ አስቀመጠች ።

https://p.dw.com/p/4TSuz?maca=amh-RED-Telegram-dwcom