Get Mystery Box with random crypto!

የሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓም የዓለም ዜና በድምጽ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለስድ | DW Amharic

የሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓም የዓለም ዜና በድምጽ
የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለስድስት ኤጲስቆጶሳት ሹመት ሰጠች። የዛሬ ተሿሚዎች ትግራይ ውስጥ እና በውጭ ሀገር ቤተክርስቲያኒቱ እና ምእመናኑ የሚያገለግሉ ናቸው ተብሏል።

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምዕራባዊ ግዛት ናያኮቫ በተባለች መንደር አንድ ወታደር ለሃዘን በተቀመጡት ሰዎች ላይ በከፈተው የእሩምታ ተክስ ቢያንስ 13 ሰዎችን መግደሉ ተሰማ። ከሞቱት ውስጥ ዘጠኙ ህጻናት ናቸው።

ሩስያ በኦዴሳ ከተማ ከተማ ዛሬ በፈጸመችው የሚሳይል ጥቃት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስና ትምህርት ማዕከል የተመዘገበውን ታሪካዊው የዩክሬይን ኦርቶዶክስ ካቴድራል ማውደሟን ክየቭ አስታወቀች፤ ድርጊቱንም "የጦር ወንጀል" ብላዋለች።

ዩክሬይን በሩስያ በሃይል ከተያዙባት መሬቶች ግማሽ ያህሉ ማስመለሷን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ። https://p.dw.com/p/4UI2P?maca=amh-RED-Telegram-dwcom