Get Mystery Box with random crypto!

​​ የጠፋው ሬሳ #ክፍል ሀያ-ሶስት ...የማየውን ማመን አቃተኝ ኮቴውን ወይም ድምፁን አልሰማሁ | Emoji feelings🦋

​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል ሀያ-ሶስት

...የማየውን ማመን አቃተኝ ኮቴውን ወይም ድምፁን አልሰማሁኝም ግን አጠገባችን ተገኝቷል ቅድስቴ እንዳለችውም ይህ ሰው በአንድ መናፍስታዊ አገዛዝ ስር እንዳለ ውስጤ አረጋገጠልኝ...ሰውዬውን ከጀርባዋ እንደተመለከትኩት የቅድስቴ ስም ጠርቼ ወደራሴ ጎተትኳት ተያይዘንም እሷ ከላይ እኔ ከታች ሆኜ ወለሉ ላይ ወደቅን አንገቴን ከፍ አድርጌ ስመለከት ሰውዬው የለም ትቶን እንደሄደ አስቤ ደስ አለኝ "አይዞሽ ቅድስቴ ተርፈናል ሌሎቹን ፈልገን ከዚ እንሄዳሀን" አልኳት ነገር ግን መልስ አልሰጠችኝም...አይርገበገብም እንጂ አይኖ ተከፍቷል በጣም ግራ ተጋባሁ ሰውዬው ምንም ሲያረግ አልተመለከትኩትም ነበር እና ምን ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል...ደግሜ ደጋግሜ ስሟን ጠራሁት ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችኝም ነበር ፊቷ ላይ የመጎዳት ነገር አይነበብበትም ቀስ አድርጌ ከላዬ ላይ አንስቼ ወገቧን ደገፍ አድርጌ በጀርባዋ ሳስተኛት የዛገ የሚመስል ስለታማ ብረት በጉሮሮዋ ወጣ ከድንጋጤዬ የተነሳ እጅግ በብዙ ድምፅ ጮውኩኝ ደጋገምኩት አይኔንም ከሷ ላይ መልሼ በዳዴ ከአጠገቧ ሸሸሁ አንዱ ጥግ ላይ ሆኜ ተኮራምቼም አነባሁኝ ያ አረመኔ ሰውዬ እኔን ለምን እንደማይገድለኝ ትንግርት ሆኖብኛል... ቅድስቴ ወለሉ ላይ እንደተንጋለለች ነው እኔ ደግሞ እሷን ማየት ፈርቼ ከአንዱ ጥግ ላይ ነኝ...አሁን መቋቋም የማልችለው ገደብ ያጣ ቁጣ ውስጤ መንፎልፎል ጀመረ ግን ደግሞ የቅድስቴን ሞት ሳይ ጓደኛዬን ያላተረፈ እልህ ብዬም ራሴን አኮማሽሻለሁ...የተቀመጥኩበት ሆኜ ራሴን ከግድግዳው እያጋጨሁ ምንም ሳላወራ መራር እንባዬን አፈሰስኩ አለቀስኩ የእንባ ከረጢቴም እስኪደርቅ ድረስ...ክፉኛ ራስ ምታትም ስቃዬን አበዛው...ሳላስበው እዛው ከተቀመጥኩበት ስፍራ እንቅልፍ አሸለበኝ በስቃይ የዛለ ሰውነቴ ከዚ በላይ የመቆየት አቅም አልነበረውም ነበር...ይመስለኛል ለሰዓታት ያህል ቁጭ ባልኩበት ስፍራ ተኝቻለሁ...እንደነቃሁም እንደምንም ብዬ ወደ ቅድስቴ በድን ዞር አልኩኝ ነገር ግን ቅድስቴ አልነበረችም ነበር ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ አይኔንም ጠራርጌ በድጋሜ ተመለከትኩ ቅድስቴ ፈፅሞ የለችም...እንደ ፈጣሪ ቃል የጓደኞቼ በድን ከአፈር ሳይዋሃድ በሰው አውሬ ተበልቶ አለቀ ይሄ ምነኛ የሚያም እና የማይሽር ቁስል እንደሆነ እኔና እኔ ነኝ የምናውቀው...ቀስ ብዬ በድኗ ወደነበረበት ወለል ተጠጋሁ መሬት ላይ እየጎተተ እንደወሰዳት የደም ምልክቱ ያሳያል የጣልኩትን ቢላ አንስቼ ደሙን እየተከተልኩ ቀስ ባለ እርምጃ መሄድ ጀመርኩኝ እነሱ ወዳሉበት ክፍል በሚወስደው በር በኩል ይጠቁማል የደም ምልክቱ እኔም ያለ አንዳች ፍራቻ በተረጋጋ እና ማስተዋል በሞላበት እርምጃ መጠጋቴን ቀጠልኩ..."ከሞት በላይ ምንም ሊመጣ አይችልም ቀኔ ከሆነ ትንታም ይገለኛል አይደለም ይሄ ክፉ አረመኔ ሰው" እያልኩኝ ውስጤን ለጭካኔ እያነሳሳሁ እና እያጀገንኩ ገዳይን ለመግደል በተጠንቀቅ ራሴን አዘጋጀሁ...የደሙ ምልክት ብዙ ጋውኖች ወደተሰቀሉበት ክፍል ይጠቁማል የሮቤል በድን ወደነበረበት...አሁን በጣም ድንጋጤዬ መጣ እነዛ ንፋስ የሚቆርጡ የሚመስሉ ስለቶች የቅድስቴ ገላ ላይ ሊያርፉ እንደሆነ ገብቶኛል ይሄኔ እርምጃዬን ጨመር አድርጌ ግን ደግሞ ጥንቃቄ ሳይለየኝ ወደ በሩ ተቀረብኩኝ አልተዘጋም ነበር ገርበብ እንዳለ ነው አንገቴን ወደ ውስጥ ቀስ ብዬ ላኩት ሰውዬው ለሮቤል ሲያረግ የነበረውን ሁሉ አድርጓል ከጋወን እስከ ጓንት ድረስ ትጥቁን አማልቷል የቀረው ቢኖር ያ የዋይታ እና የሰቆቃ ነገር ግን እሱን የሚያስደስተው እና ሰላም የሚሰጠው ድምፅ ብቻ ቀርቷል እንደጠበኩትም ያንን የሚሰቀጥጥ የስቃይ ዋይታ ከፈተው አሁን በይበልጥ ከፊል ሰውነቴን ወደ ውስጥ አስገብቼ ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ ለሮቤል እንዳረገው ሁሉ ለቅድስቴም ዘይት ጥዷል እያፏጨ እና እየተንቀሳቀሰ ስለቶቹን መመራረጥ ጀመረ በድንገት ዋይታው ፀጥ አለ ሰውዬውም ከእንቅስቃሴው ተገታ ባለበትም ቦላ በአርምሞ ቆመ እኔም አመሉን ስለማውቀው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረኩም ነበር ትንሽ እንደቆየ ጩኸቱ ጀመረ በዚ ጊዜ የሰውነቴ ክብደት በበሩ ቀድሞ በገባው እግሬ ላይ ስለበር ድካም ተሰማኝና ራሴን ለማሳረፍ ወደነበርኩበት ቦታ ልመለስ ስል አነስ የምትለዋ ሴትዮ ከፊት ለፊቴ ነጭ ጋወን ለብሳ የብረት መዶሻ ይዛ ቆማለች በጣም ደነገጥኩኝ ደነዘዝኩኝም ሴትየዋ ጊዜ አልፈጀችም ነበር ወዲያውኑ በመዶሻው ግንባሬን ስትለኝ በሩን በርግጄ ወለሉ ላይ ተዘረጋሁ እይየተስለመለመ ወደላይ ስመለከት አረመኔው ሰውዬ መጥረቢያውን ከፍ አረጎ መሀል ጭንቅላቴ.............

......ይቀጥላል...........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ አራት እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ


Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን