Get Mystery Box with random crypto!

​​‍ የጠፋው ሬሳ (ምዕራፍ ሁለት) ክፍል-ሁለት ፡ ...አይኑ ደም መስሎ በእጁ በደም የተጨማለቀ | Emoji feelings🦋

​​‍ የጠፋው ሬሳ
(ምዕራፍ ሁለት)
ክፍል-ሁለት


...አይኑ ደም መስሎ በእጁ በደም የተጨማለቀ ቢላ ይዞ ፊት ለፊቴ ቆሟል ከጀርባው የሚንጠባጠበው ደም ወለሉን አጨቅይቶታል በሱሪው ላይ ሳይቀር ይፈስ ነበር ይህ ሰው በሰው ሀይል የሚሞት አይደለም ብዬ ደመደምኩ ከንፈሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ ቀስ እያልኩ ወደሗላ ለመሸሽ መሞከር ጀመርኩኝ እዛው የቆመበት ቦታ ሆኖ አይኑን እኔ ላይ ተክሎ አንገቱን ወደ ግራ ወደቀኝ እያደረገ ይመለከተኝ ጀመር እንዴት ፈጥኖ እርምጃ እንዳልወሰደብኝ አንገቴንም እንዳልቀላው ግርምት ሆኖብኛል አራቴ እንደተራመድኩ እሱን የጣልኩበት ጠረጴዛ ጋ ደረስኩ ከዚ በሗላ ለመሸሽም አመቺ አይደለምና ዝም ብዬ በፍርሃት ተውጬ ቆምኩኝ ፀጉሬ ተፈቶ በከፊል ፊቴን ሸፍኖታል የድነሸጋጤ ላብ ያረጠበው ጉንጭና ግንባሬ ላይ ተለጥፏል...ቆሞ ሲመለከተኝ የነበረው አረመኔው ሰው አሁን ወደኔ መምጣት ጀምሯል ይዞት የነበረውን ቢላ ወለሉ ላይ ጥሎ የስንት ሰው አንገት የቀላበትን የደም ጥማተኛውን መጥረቢያ አንስቶ ወደኔ መጠጋቱ ቀጠለ አይኔን ጨፍኜ የአምላኬን ስም ጠራሁ "ዛሬም በአርያም ህያው ሆኖ ስለኔ በሚማልደው ስለ ምድር ሀጢያት በጨካኞች በፈሰሰው ደምህ ነፍሴን ከበደልና ከሀጢያት አንፅተህ በመንግስትህ አስበኝ በልጅህ ልጅነትን አግኝቻለሁና የምህረት አባቴን አንተንም ብቻ በድያለሁና ይቅር በለኝ" ብዬ ፀሎቴን አድርሼ አይኔን ገለጥኩኝ መጥረቢያውን በእልህ አጥብቆ ይዞታል አሁን ነፍሴ መጨነቋን ትታ መች ከስጋዬ እንደምትለይ በጉጉት እየጠበቀች ነው ሞት ፊትለፊቴ ቆሞ ውስጤ ግን ሰላም ይሰማኛል...በቀኝ እጁ የያዘውን መጥረቢያ ወደ ግራ እጁ ቀየረው ከዛም ወደኔ ተጠግቶ በከፍተኛ ሀይል በጥፊ መታኝ አወዳደቄን ስላልተቆጣጠርኩት በጭንቅላቴ ከወለሉ ጋር ተላተምኩኝ እዛው ወለሉ ላይ እንዳለው አይኔን ስገልጥ የማየው ምስል ድብዝዝ ያለ ነበር አይኔ እየተስለመለመ ተከደነ የሚሆነው እስከማይታወቀኝ ድረስ ራሴን ሳትኩኝ...ብቻ እግሬን ይዞ ሲጎትተኝ የሆስፒታሉ መብራት እንደለመደው ሲበራና ሲጠፋ በጭላንጭል ይታየኛል ከደቂቃዎች በሗላ ግን ምንም ማየት አልቻልኩም...ረዘም ላለ ደቂቃ ራሴን መሳቴ የታወቀኝ አምልጬ የየወጣሁበት ሁለቱ ሴቶች ያሉበት ክፍል ራሴን ሳገኝ ነው ይመገቡበት ከነበረው ክፍል ግን የተለየ ነበር እንደነቃሁ ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ ግን ከሰመመን መንቃቴ መሰለኝ ያስተዋልኩት ነገር የለም አሁንም ራሴን እያዞረኝ ነው በእጆቼ ጭንቅላቴን ልደገፍ እጄን ላነሳ ስል አልንቀሳቀስ አለኝ ከጭንቅላቴ ትንሽ ቀና ብዬ ስመለከት እጄ ከወገቤ ጋር ከተኛሁበት የብረት አልጋ ላይ የፊጢኝ ታስሯል...ሰፋ ያለ ጥቁር ቀበቶ ነበር...ሶስቦታ ላይ ታስሬያለሁ ደረቴ ወገቤጋና እግሬ ጋር ነበር አለለመሞቴ የታወቀኝ አሁን ነው በህይወት መኖሬ እጅግ ደንቆኛል አሁን ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ እንደኔ የታሰሩ ሁለት ሰዎች ይታዩኛል ነገር ግን ማንነታቸውን መለየት አልተቻለኝም አጠገቤ ካለው ወዲያኛው ክፍል ውስጥ በአቧራ ከነተበው መስታወት አሻግሬ ለመመልከት ሞከርኩ ሁለቱ ሴቶች ከዛ አረመኔ ጋር እየተጨቃጨቁ ይመስለኛል ጠፍሮ የያዘኝን ቀበቶ ለመፍታት ክፉኛ ታገልኩኝ እራሴንም እስክጎዳ ድረስ ተፍጨረጨርኩ ተወራጨሁ ግን ከኔ አቅም በላይ የጠነከረ ነበርና ምንም ማረግ አልቻልኩም አቅሜን ሳውቅ ፍርዴን መጠበቅ ጀመርኩ አረመኔውና ሴቶቹ አሁንም ይጨቃጨቃሉ በኔ ነገር እንደሚሆን ውስጤ እየጠረጠረ ነው ልብሱን አውልቆ የጀርባ ቁስሉን አሳያቸው ትንሿ ሴትም ሁለቱን እዛው ያሉበት ቦታ ትታቸው ክፍሉን ለቃ ወጣች ወዴት እንደሆነ ባላውቅም በድንገት እኔ ከታሰርኩበት ክፍል ውስጥ "ሜርሲ" የሚል ድምፅ ተሰማኝ በአቧራ ከነተበው መስታወት ባሻገር የላኩትን አይኔን እና ቀልቤን መለስ አድርጌ አብረውኝ ከታሰሩት ሁለት ሰዎች መሃል ስለመከት...ይቀጥላል