Get Mystery Box with random crypto!

​​‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት (ክፍል ሶስት) ፡ ...አይኔ ያየውን ማመን አቃተኝ 'ባርሳ' ነበ | Emoji feelings🦋

​​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
(ክፍል ሶስት)

...አይኔ ያየውን ማመን አቃተኝ "ባርሳ" ነበረች ድንጋጤና ደስታ በአንድ ላይ ተቀላቀሉብኝ ግን አንዲትም ቃል አልተነፈስኩም እሷም እንደኔ የፊጥኝ ታስራለች ፊቷ ላይ የደም ነጠብጣብ ይታየኛል አይን አይኔን እያየች አንባዋ ቁልቁል ወደ ጆሮዋ ይወርዳል አሁን ያለሁበት ሁኔታ ጥሩ ባይሆንም ግን የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል "በአንበሶች ጉድጓድ የተጣለውን ዳንኤልን ያየ አምላክ አይኑም ክንዱም ለኔ እንደማይዝሉ አምናለሁ" ብዬ ለራሴ አውርቼ ባርሳን እያየሁ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ ፊቴን ከሷ ላይ መልሼ በአቧራ ካደፈው መስታወት አሻግሬ ተመለከትኩ አነስ ምትለዋ ሴት የተለያዩ የህክምና መስጫ መድሃኒቶችን ይዛ አረመኔውን ሰውዬ ካላከምኩህ ብላ ትሟገተዋለች እሱ ደግሞ አለመፈለጉን በምልክት ያሳያታል ምን እንደምትለው ለማወቅ ቢቸግርም ብቻ ብዙ ነገር እያወራችው ነው ከወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ የሆነ ነገር ማብሰልሰል ውስጥ የገባ ይምስላል ግራ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ የቀኝ እጁን ደግሞ አፉ ላይ አድርጎ ሌባና መሃል ጣቱን ከፍና ዝቅ እያደረገ ይንጎራደዳል ትልቋ ሴትዮ ቁጭ ብላ ትመለከተዋለች ብቻ አንዳች ነገር እያሰበ ነው ትኩረታቸው ወደኛ ሊሆን እንደማይችል በተረዳሁ ጊዜ ወደ ባርሳ ተመለስኩኝ እሷ አሁንም ወደኔ እየተመለከተች ነበር "ባርሳ" ብዬ ጠራሗት እጅግ ዝግ ባለ ድምፅ "ሜርሲ ደና ነሽ ደግሜ አይሻለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከመሞቴ በፊት ስላየሁሽ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ" አለች በእንባ ሳግ በሚቆራረጥና በለዘበ ድምፀት "ሽሽሽሽ እንደዚ አትበይ ባርሳ አይዞሽ ተስፋ አትቁረጪ እስካሁን የቆየሽው ለምክንያት ነው እሱ እኛን ከመግደሉ በፊት ራሳችንን ገለን ልንጠብቀው አይገባም አይዞሽ ባርሳዬ" ስላት ከንፈሯን እየነከሰች እንባዋን ለማቆም መጣር ጀመረች የሷ መበርታት ለኔም አቅም ነው...በድጋሜ አይኔን ወደ ሰዎቹ መለስኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያው አይኔን ወደ ክፍሉ መልሼ የክፍሉን በር ተመለከትኩ ማንም አልመጣም ባርሳን ዝም እንድትል ነግሪያት ለደቂቃዎች ፀጥ አልን ግን አንዳች ነገር አልተከሰተም ለምን እንደው እንጃ ከአይኔ መሰወራቸው ጨንቆኛል "ባርሳ ይሄስ ማነው" ብዬ ጠየኳት አጠገቧ የተኛውን ለማየት ያልተመቸኝን ክፍሉ ውስጥ ያለውን ሌላኛውን ሰው "ባባ ነው" አለችኝ በጣም እንዳዘነች ፊቷ አብዝቶ ይናገራል "ምን ሆኖል በጣም ተጎድቷል እንዴ..." እያልኩኝ ጥያቄዬን ሳልጨርስ ከፍ ባለ ድምፅ "ግደላት" የሚል ድምፅ ሰማሁ አይኔን ወደ መስታወቱ መለስኩኝ ትንሿ ሴትዮ ነበረች ለአረመኔው ሰውዬ ስታወራ የነበረችው ትልቋ ሴት ቁጭ ብላ ትመለከታቸዋለች ወዲያውኑ ሰውዬው እርምጃውን አፍጥኖ በእልህ እኛ ወደነበርንበት ክፍል ሲምዘገዘግ መጣ በሩንም ብርግድ አርጎ ገብቶ ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ ከዛም በራስጌ በኩል ሆኖ የተኛሁበትን አልጋ እየገፋ ወደ ውጪ ይዞኝ ወጣ ባርሳ አይን ላይ ያየሁትን ፍቅርና ፍራቻ ቃል አይገልፅልኝም በትንሿ ሴት መሪነት ወደ ሌላ ክፍል ተወሰድኩኝ ምንም አላልኩኝም ነበር...ክፍሉ ውስጥ ገባሁ እስከዛሬ ያልተመለከትኩት በስለት የተሞላ አስፈሪ እና አሰቃቂ ቦታ ነው ሰውዬው የታሰርኩበትን ቀበቶ መፍታት ጀመረ ልክ እንደጨረሰም አንጠልጥሎ ከአንድ የማይንቀሳቀስ ተለቅ ያለ የብረት ወንበር ላይ አስቀመጠኝ...ወዲያውኑ እጄን ለክንድ ማስቀመጫ ተብሎ ከተሰራበት የወንበሩ ክፍል ጋር አጥብቆ አሰረው ወረድ ብሎም ከመዳፌ ትንሽ ከፍ ብሎ በድጋሜ አሰረኝ እግሬንም እንዲሁ ከወንበሩ ጋር አሰረው አስሮ እንደጨረሰ ከኔ ራቅ ሲል ክፍሉን መመልከት ጀመርኩኝ የተለያዩ የእጅ እና የእግር ጣቶች በየቦታው ተንጠባጥበዋል ጥፍሮችም ጭምር ከተቀመጥኩበት በስተ ቀኝ በኩል ያየሁት ነገር ከምንም በላይ ሰቅጥጦኛል ከአንድ ሰርቢስ ላይ በአንድ ላይ የተቀመጡ የአይን ኳሶች ይታዩኛል በሌላኛው ሰርቢስ ላይ ደግሞ ጆሮና ምላስ ተቀምጧል አጥወለወለኝ አንገሸገሸኝም የማረገውና የምሆነው ጠፋኝ ሆዴ ተላወሰ አስመለሰኝም እዛው በተቀመጥኩበት ራሴ ላይ ለቀኩት ቀና ብዬ ስመለከት ከበላዬ የተለያየ አይነት ቅርፅ ያላቸው መርፌዎች ይታዩኛል ዶክተሮች ለህክምና የሚጠቀሙት መብራትም አለ ሰውዬው ጋውን ለብሶ ወደኔ መጣ የተቀመጥኩበትንም ወንበር ትንሽ ከፍ አድርጎ ወደሗላ አንጋለለው አሁን ካሁን ወደኩኝ ስል ወንበሩ ግን አልወደቀም ነበር አሁን ለመወራጨትም ሆነ ለምንም የማያመች አቀማመጥ ነው ያስቀመጠኝ ዶክተሮች ለቀዶ ጥገና የሚጠቀሙበትን መብራት አበራው አይኔ እሱን መመልከት አልቻለም ነበር ጨፈንኩት ይህ ሰው ሊያሰቃየኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው በቀሉን ለመመለስ ይመስላል ከዛም ክፍሉ ውስጥ ይበራ የነበረውን መብራት አጠፋው አይኔን ከፍቼ ግራ ቀኜን ስመለከት አንዳች አልታየኝም የመብራቱ ጉልበት ከፍተኛ ነበር እዛው ባለሁበት አንደበቴን ዘግቼ ፀጥ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ ከሰከንዳት በሗላ ሰውዬው ወደኔ ሲመጣ የእግር ኮቴው ተሰማኝ...ይቀጥላል