🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ክፍል-አራት የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...ከኮቴው ጋር ከ | Emoji feelings🦋

​​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
ክፍል-አራት
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)

...ከኮቴው ጋር ከብዙ ስለቶች መሀል ስለት ሲፈለግ የሚሰማው ድምፅ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ ከዛም አብዝቶ ወደኔ
ተጠጋ አንዳች ድቡልቡል ነገር አፌ
ውሴጥ አሰገባ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ
አይኔን እስከመጨረሻው ግልጥ አድርጌ
ከፈትኩት ነገር ግን ከመብራቱ በቀር
አንዳች አልታየኝም አፌ ውስጥ የከተተው ነገር ማሰሪያ ነበረውና
ከጭንቅላቴ ጋር የፍጢኝ አሰረው መጮህ እየፈለኩ ግን አልቻልኩም ፍፁም ለስቃይ የታሰበ ነገር ነው አይኖቼን ዘግቼ "የልጅህ የክርስቶስ ደም
ከበረዶም ይልቅ ከበደል ያነፃልና በደል
መተላለፌን በአሪያም ዛሬም ድረስ
ህያው ሆኖ ስለኔ በሚቃትተው ደምህ
አንፃኝ በመንግስትህም አስበኝ" ብዬ
የመጨረሻ ቃሌን ለአምላኬ በልቤ አንደበት ነገርኩት...አይኔን ከድኜ ሞቴን
በመጠባበቅ ነኝ...ድንገት ሰውዬው ቀረብ ብሎ ከላይ የለበስኩትን
በመቀስ እየቆራረጠ ከላዬ ላይ ገፈፈው
በጡት ማስያዣ ብቻ ቀረሁ በድጋሜ ሱሪዬንም መቅደድ ጀመረ ጫማዬንም
አወለቀው ልክ ካልሲዬን ሲያወልቀው
እግሬ ላይ ከነበረው ቁስል ጋር ተጣብቆ
ነበርና ክፉኛ አመመኝ አሁን እርቃኔን ነኝ
ከአይኖቼ የሚፈሰው እንባ ቁልቁል ወደ
ጆሮዬ ይምዘገዘጋል...እላዬ ላይ የበራው
መብራት ለኔ ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ ሰውነቴን አግሎታል መላ አካሌን ላብ
ሲጠምቀኝ ይታወቀኛል...ግን ከዚ ሙቀት ውስጥ እላዬ ላይ የደፋው እጅግ
ቀዝቃዛ ውሃ አወጣኝ...የእግሮቼ አውራ ጣቶች ላይ ምን እንደሆን እንጃ ቁንጥጥ
አድርጎ እንዲይዘኝ አደረገ...ሰውዬው ከኔ
ርቆ ሲሄድ ይሰማኛል ግን ከክፍሉ እንዳልወጣ ተረድቻለሁ በመቀጠልም እንደ ማብሪያና ማጥፊያ አይነት ድምፅ
ያለው ነገር ተሰማኝ ቀመቅፅበት
መላ አካላቴን ለሰከንዶች ያህል አርገፈገፈኝ ወዲያውኑ አቆመው መተንፈስ አቃተኝ በአፍንጫዬ ብቻ የሚገባው አየር አልበቃሽ አለኝ አሁንም
በድጋሜ የማብሪያ ማጥፊያውን ድምፅ
ሰማሁት እንደገና አርገፈገፈኝ አሁን ትንሽ
ቆየት አድርጎብኛል ከዛም አጠፋው ደም ስሮቼ በአየር እጦት ክፍኛ ተወጥረዋል
አይኔ አብዝቶ ፈጠጠ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ከባድ ስቃይ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደፈለኩ የምምገው አየር አብዝቶ ናፈቀኝ ከየትም
ላላመጠው ነገር...በዚ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ሰውዬው ሲራመድ በድጋሜ ተሰማኝ ለቅፅበትም ቢሆን ትንሽ መረጋጋት ተሰማኝ...ነገር ግን
ብዙ አልቆየም ነበር ያንን ቀዝቃዛ አካልን
የሚቆርጥ ውሃ በላዬ ላይ ከለበሰብኝ
ከተቀመጥኩበት ብረት ወንበር ጋር የተነካካው የአካሌ ክፍል ውሃ ሲነካው
ህመሙን መቻል አቃተኝ...ወዲያውኑ ያንን ማብሪያ ማጥፊያ በድጋሜ ተጫነ
ውሃው ስቃዬን አባሰው...ያበራውን ሳያጠፋ እየተርገፈገፍኩኝ ውሃውን
ይጨምርብኝ ጀመር ረዘም ላሉ ሰከንዶች
ከቀጠለ በሗላ አጠፋልኝ...አሁን ምንም
የማረግ አቅም አልነበረኝም አየር የተባለ
ጉሮሮዬ ጋር አይደርስም አይኔ ሲገለበጥ
ይታወቀኛል ግን ያልጠበኩት ነገር ሆነ
ሰውዬው አፌ ውስጥ ያስገባውን ነገር
አወጣልኝ ወዲያውኑ አስመለሰኝ እጅግ
ፍጥነት ባለው አተነፋፈስ አለከለኩኝ እየደጋገመ ያስመልሰኛል...አልቻልኩም
አቅሜ ፈፅሞ ተሟጧል...የክፍሉን ዋናውን መብራት አበራውና አይኔ ላይ ተደንቅሮ የነበረውን አጠፋው ከአንዱ ጥግ ቆሞ አተኩሮ ይመለከተኛል ግራ
የተጋባ ይመስላል አይኖቹ አይረገበገቡም የተሰፋፋው ፊቱ ፈፅሞ
አይፈታም ደም የለመዱ እጆቹ ርህራሄ የላቸውም የሰው የማይመስለው ልቡ ምህረትን አያውቅም ብቻ ዝም
ብሎ ይመለከተኛል ለምን እንደሆነ ለኔ ፍፁም ግራ ነው...እንደዚ እንደተፋጠጥን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ወደራሴ እየተመለስኩ ስመጣ የራሴ ስጋ ሽታ
ሸተተኝ በኤሌክትሪክ ሾክ ገላዬ ተጠብሶ
ነበር ትንሽ እንደቆየ ገላዬ ላይ ያለው እርጥበት ሲደርቅ ወደኔ መራመድ ጀመረ
የተዘቀዘቀውን ወንበር እንደመጀመሪያው
አስተካክሎ አስቀጠው ከውንበሩ
ጋ የታሰረውን የእጅና የእግር ማሰሪያ ፈታልኝ ከዛም ከፊት ለፊቴ ሁለት እጄን
ይዞ እግሩን ከፍቶ ቆመ ጭንቅላቴን
መሸከም አቅቶኝ አጎንብሻላሁ እጄን በእጁ እንደያዘ ለሰከንዶች ፀጥ ብሎ ከቆየ በሗላ ሳላስበው...ይቅጥላል