Get Mystery Box with random crypto!

‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ክፍል-ሰባት ፡ ....ወደ ቀልቤ ሳልመለስ ደቂቃዎች ተቆጠሩ የሚሆነ | Emoji feelings🦋

የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
ክፍል-ሰባት


....ወደ ቀልቤ ሳልመለስ ደቂቃዎች ተቆጠሩ የሚሆነውን በማላስተውልበት ሁኔታ ሰከንዳት
ብዙ ተጓዙ ነገር ግን በዛሁ አልቀረሁም
ያለሁበትን ካስረሳኝ ሰመመን ነቃሁ
በደም የተጨማለቀ አይኔን ለመግለጥ
ሞከርኩኝ ግን አልቻልኩም
ምንም እንኳ ብነቃ አካሌን መዘዝ
ተስኖኛል የቅድሙ ቅዝቃዜ ፈፅሞ
የለም ግን ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን
የኔ መደንዘዝ ነው...ሰውነቴ ስለሚፈጠርበት ነገር ምላሽ ለመስጠት አቅም የለውም ነቅቼም
በድን ሆኛለሁ...በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ደቂቃዎች አብዝተው ተጓዙ
እናም ሰውነቴን ለማገላበጥ ነቅነቅ
ስል ከጭንቅላቴ ጋር እንደ ትራስ የሚመስል ነገር ተሰማኝ በጣም
ደነገጥኩኝ ባዶ ወለል ላይ ነበር የተዘረርኩት እና ከየት መጣ ማንስ
አመጣው ይሄን ጥያቄ እስክመልስ
ድረስ እንቅስቃሴዬን ገታሁ...
ደም
የተጋገረበትን አይኔን በመዳፌ ለማፅዳት ሞከርኩ ነገር ግን ደርቆ
ነበርና ቀላል አልሆነልኝም...ያለውንም
ሁናቴ በእጆቼ መዳፍ ለማጣራት እጄን
ወደ ትራሱ ሰደድኩት ነገር ግን አስቤ
እንደነበረው ትራስ አይደለም...በጣም
ደነገጥኩኝ የሰው እግር ነበር እጄን
ወደነበረበት መለስኩኝ ልቤ ክፉኛ
ተወራጨ አንድም በደስታ አንድም
በጭንቀት...ደስታው የሚረዳኝ ሰው
የመጣ መሰለኝ ጭንቀቱ ደሞ ያ ሰው
ማነው የሚለው ነበር...ከአንደበቴ ቃል
አውጥቼ አወራ ዘንድ አልቻልኩም
ቃሎቼ ከአንደበቴ ሳይወጡ ከንፈሬ
ላይ ይመክናሉ ምላሴ እንደቀድሞው
አይታዘዝም ወይ አጠገቤ ያለው ሰው
ራሱ ቢያወጋኝ ምን አለ ወይ ደግሞ
የአይኔ ሽፋሽፍቶች ከብሌኔ ቢሸሹ ምን ነበር ይህን የኔ ደራሽ ባየሁት አልኩኝ
መዳፌ አላረፈም ደጋግሜ ዳሰስኩት
ነካካሁት ከናፍሬ ባይሸሽም ነፍሴ ግን
ከልቧ እየሳቀች ነው የሆነ ሰው ብቻ
መድህኔ ነው ልበለው ያንን አረመኔ
ነፍሰ በላ የሰው ስጋ ጥማተኛውን
አፈር እንዳስበላው ይሰማኛል ነፍሱንም ስለ ጠፉት ነፍሶች ብሎ
እንደቀጣት ውስጤ ይነግረኛል የጓደኞቼን በቀል የስጋቸውን ደም
የነፍሳቸውን ሲቃ አንዱ አዳኝ(ላልቶ)
የስቃዩን እና የሰቆቃውን ምንጭ
እንዳደረቀ ይሰማኛል...አካሌ ከነበረበት ድንዛዜ እየወጣ ነው መሰል ቅዝቃዜው ይሰማኝ ጀምሯል ከቅዝቃዜው ይልቅ ግን
ውስጤ ድረስ የተሰማኝ ፀጉሬ መሃል
የሚርመሰመሱት ጣቶች ነበሩ
ፍፁም ሰላም ሰጡኝ ብዙ ተስፋን ሞሉኝ ፀጉሬ ከዚ በፊት ተዳብሶ
እስከማያውቅ እንግዳ ሆነብኝ ጣቶቹ
የጭንቅላቴን ቆዳ ሲነኩት ይጎረብጣሉ
አይመቹም ግን እስከዛሬ ሲነኩኝ ከነበሩት ከለሰለሱ መዳፎች ይልቅ ልዩ
ደስታን ሰጥተውኛል የተለየ ስሜትም
አላቸው፡፡
ለማንም አሳልፎ የማይሰጠኝ ብርቱ
ክንድ አጠገቤ እንዳለ ነፍሴ አመነች
እኔም ተስማማሁ...ጣቶቹ ፀጉሬ መሃል
ሲዋኙ እኔ በምናብ ክንፍ እላለሁ በፀደይ ወራት ውስጥ በለመለመ መስክ ላይ ለዘብ ባለች ፀሃይ ታጅቤ
ከልካይ በሌለው ሜዳ ላይ ስቦርቅ
ይታየኛል ግን ብቻዬን አልነበርኩም
አንድ የማላውቀው ግን ደግሞ
ደስታዬን እጥፍ ያደረገ ወጣት አብሮኝ
አለ አላወራውም እሱም አያወራኝም
ግን አንዳችን ላንዳችን ደስታ ነበርን
ፀሃይ አዘቅዝቃ ወደ ጎጆዋ ስትገባ እሱ
ግን ከኔጋ ነበር ከፀሃይ ብርሃን ይልቅ
ለኔ ያስፈልገኛል ግን አላውቀውም
አላወራውምም...ከሄድኩበት የሰመመን ደስታ መለስ አልኩኝ
በጣቱ ንክኬ በመዳፉ መዳሰስ ሰላም
የሚሰጠኝ ይህ ማነው እግሮቹ ላይ
ተኝቼ ምንስ ያኩራራኛል እንደ መከታዬ ያሰብኩት ይህ ሰው ማነው?

ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከደባበሰኝ በሗላ
እግሩ ከጭንቅላቴ ስር ሲነሳ ተሰማኝ
አትሂድ ልለው ብዬ አልቻልኩም...
አንደበቴ ታስሯል የክንዱ መፈርጠም ፆታውን ነግሮኛል አይቼ እንዳለየው
አይኖቼ ተጋርደዋል ባለሁበት
ሆኜ እጄን እየዘረጋሁ ዙሪያዬን ዳሰስኩ አንዳች አልነበረም ግን ከተኛሁበት ለመናሳት ስጥር ድግፍግፍ
አድርጎ አነሳኝ አሁንም አጠገቤ እንዳለ
ታወቀኝ ጥሎኝም እንዳይሄድ ባለችኝ
ኢምንት አቅም ያዝኩት እሱም ከኔ አልሸሸም...ግን ማነው?....ይቀጥላል

እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን