🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ክፍል-ስምንት የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...ልክ እንደ ህ | Emoji feelings🦋

​​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
ክፍል-ስምንት
የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር)

...ልክ እንደ ህፃን ልጅ አቅፎኝ ሲራመድ
ይታወቀኛል ወዴት እንደሚወስደኝ
ባላውቅም ልቤ ግን ለሰከንድ አልጠረጠረውም ነፍሴም በብዙ ታምናበታለች....እርግት ያለው የእርምጃው ድምፅ ደስታን ይሰጠኛል
ትንሽ እንደተጓዘም ከአንድ ስፍራ በጥንቃቄ አስቀመጠኝ ቀስ እያለም የለበስኩትን ልብስ አንድ በአንድ ማውለቅ ጀመረ ከቁስሌ ጋር ተጣብቆ የነበረው ሲነሳ ልቤ ክፍል እስክትል ያስጨንቀኛል፡፡
እርቃኔን ማንም አይቶኝ ስለማያውቅ በጣም ደነገጥኩኝ ጡቶቼን በእጆቼ ሸሸኳቸው ግን እሱ ቃል ሳያወጣ
በእጆቹ መዳበስ አረጋጋኝ ዝም ብዬም
ቁጭ አልኩኝ የተመሰቃቀለውን ፀጉሬን
ማስተካከል ጀመረ ወዲያውኑ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ በተነከረ ፎጣ ገላዬን
ማፅዳት ጀመረ ህመም እንዳይሰማኝ
እጅግ ተጠንቅቆ...ከላዬ ላይ ያፀዳውን
ደም አንዳች ነገር ውስጥ ሲጨምቀው
ይታወቀኛል...
እርጋታ በተሞላበት ሁኔታ መላ አካላቴን
አፀዳው...ነገር ግን አሁንም ድረስ
ፊቴን አለማጠቡ እና አይኔን እንድገልፅ አለማረጉ
ጥያቄም ግርምትም ሆኖብኛል...እንዳላየው ለምን ፈለገ?
ድምፁንስ ለምን አውጥቶ አያወራኝም?
ብቻ ብዙ ብዙ ጥያቄ ውስጤ ይመላለሳል ለዚ ሁሉ ጥያቄም መልሴ
ዝም ብቻ ነው...አሁንም በድጋሜ ከተቀመጥኩበት አቅፎ አነሳኝ ከዛም
አልጋ ላይ ይመስለኛል አስቀመጠኝ...
ወዲያውኑ ቀዝቀዝ ያለ ዘይት መሳይ ነገር ቁስሌን ሲቀባኝ ታወቀኝ...ይህ ሰው
ሊያይድነኝ የተላከ መሆን አለበት
አልኩኝ...ዘይቱ ቁስሌን ሲያገኘው አነስተኛ ህመም ነበረው ግን ስቃዩን
ችዬ ዝም አልኩኝ ከጨራረሰ በሗላ
መዓዛው የሚያውድ ሙሉ ቀሚስ አለበሰኝ ከዛም የነበርኩበት አልጋ ላይ
በጀርባዬ አስተኛኝ ጭንቅላቴ ከአልጋው ወጣ እንዲል አደረገው
ቅድም ያሰረውን ፀጉሬን መፍታት ጀመረ...
በውሃ በራሳ ፎጣ ፊቴን ሸፈነው...
ለብ ባለ ውሃ ፀጉሬን ማጠብ ጀመረ ቀስ እያለ እያበጠረ በእርጋታ ማጠቡን ቀጠለ...እርጥቡ ፎጣ ፊቴ ላይ ያለው
የደም ቅርፊት ማራስ ጀመረ ይህን ሰው
እስካየው ነፍሴ አብዝታ ጓጉታለች
ፀጉሬን ከጨረሰ በሗላ አደራርቆልኝ
ቅባት እየቀባ ያበጥረው ጀመር ከዛም
በውል አሰረልኝ ሲወጣም የእግሩ ኮቴ
ተሰምቶኛል ግን ለደቂቃዎች ስጠብቀው አልተመለሰም ደቂቃዎችም ሰዓትን መተካት ጀመሩ ግን የለም
በጣም ጨነቀኝ ፎጣው ፊቴ ላይ እንዳለ ነው እኔም በጀርባዬ እንደተንጋለልኩ
ቀስ ብዬ ፊቴን በጋረደው ፎጣ የራሰውን ደም መጠራረግ ጀመርኩ
ከዛም አይኔ ተገለጠ ቀስ ብዬም ተነስቼ ቁጭ አልኩኝ ዙሪያዬን ስቃኝ
አንዳች ነገር የለም አካባቢው ከላዬ ላይ
በወረደው የደም እድፍ ተጨማልቋል
ለመውረድ ፈልጌ ቁልቁል ስመለከት
የሚያምር ነጭ ጫማ አለ ቀስ ብዬ በእርጋታ አደረኩት...
የለበስኩትንም ስመለከት እጅግ ውብ የሆነ የሀገር ባህል ልብስ ነው ያለሁበትን እስክረሳ ድረስ ደስ አለኝ
እየተሽከረከርኩም እራሴን አየሁ...
ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ጀመርኩ
ጠረጴዛ ላይ አንዳች የሚበላ ነገር
ተቀምጧል ጠጋ ብዬም አየሁት የታሸገ የዓሳ ስጋ ነው እጅግ እርቦኛል
ጥርግ አርጌም በላሁት አሁን በርትቻለሁ አካሌም ታድሷል
ያንን አረመኔ አሁን ማጥፋት እችላለሁ
ውስጤ በድጋሜ በእልህ ተሞላ
አይኔንም ወደ መውጫው ሰደድኩት
እልህ በለ፡ተሞላው እርምጃ ከክፍሉ ወጣሁ ኮሪደሩ ላይ አንዳች አይታይም
ፀጥ ረጭ ብሏል ጥንቃቄ በተሞላው
መልኩ ዙሪያዬን እየቃኘሁ
መራመድ ጀመርኩ...ፀጥታው እጅግ ያስፈራል ቀጥ ብዬ ከሴቶቹ ጋር ወደ ሚገናኝበት ክፍል አመራሁ ነገር ግን
አይኔ ከ ባርሰናይት ጋ አብረን ወደተኛንበት ክፍል ላይ አረፈ ጠጋ
ብዬም በመስታወት ተመለከትኩ
ከመኝታው ላይ ባርሳ የለችም
ያ አረመኔ አንዳች አርጓት ይሆን እን
ደው ብዬ ሰጋሁ...ክፍሉን ቅኝቼ
ፊቴን ወደሗላ ስመልስ ትንሿ ሴትዮ
....ይቀጥላል

እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን