🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​‍ የጠፋው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ክፍል-ዘጠኝ ፡ ...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች ፊቷ ላይ | Emoji feelings🦋

​​‍ የጠፋው ሬሳ
ምዕራፍ ሁለት
ክፍል-ዘጠኝ


...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች ፊቷ ላይ እልህና ቁጣ ይነበብባታል ኮስተር ብላ ከእግር እስከራሴ ተመለከተችኝ
ምንም ሳትናገር ዙሪያዬን ትዞረኝ ጀመር እኔም በልበ ሙሉነት እና
ያለ አንዳች ፍራቻ ፀጥ ብዬ ቆምኩኝ
ድጋሜ ፊለተፊቴ መጥታ ቆመች
ተጠጋችኝ አንዳች ነገር እንደሚያሸት ሰው አየር በአፍንጫዋ መሳብ ጀመረች
የለበስኩትን ቀሚስ በእጇ እየነካካች
ፈገግ ቁጣ እያለች ትመለከተኛለች
ድንገት "የሞትሽ መስሎኝ ነበር አለሽ እንዴ" ብላ ጠየቀችኝ
"አዎ አለሁኝ መኖር ስለቻልኩ ሳይሆን
ማኖር የሚችል አምላክ ስላለኝ አለሁ"
ብዬ መለስኩላት ማሽሟጠጥ በሚመስል መልኩ ከንፈሯን አንቀሳቅሳ
አንገቷን ነቀነቀች ውሰጤ የነበረው
ቁጣና ንዴት ወዴት እንደሸሸ አላውቅም ብቻ እርግት ብዬ ቆሜያለሁ
ከዛም የሆነ የረሳችውን ነገር ያስታወሰች ይመስላል ግንባሯን
ጭምድድ አርጋ ፊቴን አትኩራ ተመለከተችኝ "ማነው ስምሽ" የሚል
ጥያቄን ሰነዘረች "ሜርሲ" አልኳት ፈጠን ብዬ "ከዚ ቀደም እዚ ክፍል
ሆስፒታል ውስጥ ተመልክቼሻለሁ
ግን እንደዛሬው አልተዋብሽም ነበር
የማንን ቀሚስ እንደለበሽ ታውቂያለሽ"
ብላ ጥያቄዋን አስከተለች እኔም ዝቅ ብዬ እያየሁት "አይ አላውቅም ማን
እንዳለበሰኝም እንጃ" ብዬ ለጥያቄዋ ምላሽ ሰጠሁ ግራ የተጋባች ይመስላል
"ማን እንዳለበሰኝ አላውቅም?" ብላ ጥያቄዬን በጥያቄዋ መለሰች እኔም
የአንደበቴን ቃል ትቼ በአንገቴ ንቅናቄ
አውንታዬን አሳየሗት ከቅድሙ ይበልጥ አተኩራ ተመለከተችኝ...እኔም
ወዲያውኑ እግሯ ስር ብርክክ ብዬ
"እባክሽን ከዚ አውሬ አትርፊኝ ለውለታሽ የፈለግሽውን አደርግልሻለሁ"
አልኳት ድንገት ተቀየረችና ከፍ ባለ ድምፅ "ማንን ነው አውሬ አንድዬን ነው
አውሬ" ብላ ስትጮህ ከሌላኛው ክፍል
ሁካታ ድምፅ ተሰማኝ ከአይኔ የእንባ
ዘለላ እየወረደ ተማፀንኳት እሷ ግን
ፍንክች አልል አለች የሆነ ኮቴ እኛ ወዳለንበት ክፍል ሲያመራ ተሰማኝ
"አንድዬን ሰው ነው አውሬ ያረገው
እንጂ ሰፈር መንደሩ ያወቀው ትሁት
የተመሰገነ ልጅ ነበር ግን ሰው ብላ" ስቅስቅ እያለች ማልቀስ ጀመረች
ወዲያውኑ አረመኔው ሰው ደም የለመደ መጥረቢያውን ይዞ ድንገት
አጠገባችን ተገኘ ባለሁበት አጎነበሼ
የመጨረሻ እንባዬን አነባሁ ተንሰቅስቄ
አለቀስኩኝ ድንገት ከመሬት ሊያነሳኝ
ፈርጠም ያለ እጅ ክንዴ ላይ አረፈ
ቀና ብዬ አየሁት አረመኔው ሰው ነበር
መጥረቢያውን ጥሎ እጁን ዘረጋልኝ
እኔም በሱ ታግዤ ከመሬት ተነስቼ ቆምኩኝ ፊቱን ለተመለከተው ለመግለጽም ቃልን ነው ሚያሳጣው
እኔን ካነሳኝ በሗላ ትንሿን ሴትዮ ለማባበል ተጠጋት እሷ በአግራሞት
ሆነ ተደንቃ ትመለከተዋለች
ይመስለኛል ለምን እንዳልገደለኝ
ለኔ ጥያቄ እንደሆነብኝ ሁሉ እሷም
ጥያቄ ሆኖባታል አሁን እሱ ሴትየዋ
ወደኔ እንዳታይ ሙሉ ለሙሉ ከልሏታል
እኔም ድምፅ በሌለው አረማመድ ወዳስቀመጠው መጥረቢያ ተጠጋሁ
አባብለውኝ ከምሞት በጭካኔ ቢገለኝ
እመርጣለሁ ከዚ በላይ ለመሰቃየት
ዝግጁ አይደለሁም
መጥረቢያውን አንስቼ በሁለት እጄ ጨበጥኩት በለዘበ እርምጃም እሱን
መጠጋት ጀመርኩ ከሴትየዋ ጋ የተስማሙ አይመስሉም
እየተወረጫጩ ነው ሚነጋገሩት በኔና
በሰውዬው መሃል አንንድ እርምጃ ሲቀረን አቋቋሜን አስተካክዬ መጥረቢያውን ከፍ አድርጌ...ይቀጥላል