Get Mystery Box with random crypto!

ከታሪክ አምድ ____ #የሼክ_ኢብራሂም_ቢሊሳ_መኖሪያ_ቤት 1919E.C 1.የሼክ አብራሂም ቢሊሳ | ancient history of oromoo and oromia

ከታሪክ አምድ
____
#የሼክ_ኢብራሂም_ቢሊ_መኖሪያ_ቤት 1919E.C

1.የሼክ አብራሂም ቢሊሳ መኖሪያ መገኛ ቦታ
በድሬደዋ 03 ቀበሌ መሀል ከዚራ ነው

2.የቤቱ ታሪካዊ ዳራ

ይህ ቤት በ1919ዓ/ም በድሬዳዋ ከተማ ይኖሩ በነበሩት ግሪካዊያን ነጋዴዎች እንደተሠራ ይነገራል።
ግሪካዊው የቤቱ ባለቤት በዚህ ቤት በሚኖሩበት ጊዜ በህመም ምክንያት ለአልጋ ቁራኛነት ይዳረጋሉ በዚህ ጊዜ መታመማቸውን ምክንያት ግሪኮቹ ስለ ሼክ ኢብራሂም ቢሊሳ ባህላዊ ታዋቂ ሀኪም መሆናቹን ለታማሚው ግሪካዊውን ይነግሮዋቸዋል። ግለሰብም/የቤቱ ባለቤት/ ሼኩን ወደ ቤታቸው ያስጠሩታል ሼኩም ወደ ግሪካዊ ቤት በማቅናት በአስተርጎሚ ከሰሙት በኃላ መዳህኒት ከባህላዊ ህክምና ያደርጉላቸዋል ማለትም የቤቱን ባለቤት ያክሟቸዋል ከዚያም በኋላ ግሪካዊው ከህመማቸው ይፈወሳሉ በዚህ ጊዜ ይኖሩበት የነበረውን ይህን ቤት ለሼክ ኢብራሂም ቢሊሳ በስጦታ እንዳበረከቱላቸው እስካሁን ድረስ በቤቱ ውስጥ የሚኖሩት የሼህ ኢብራሂም ቢሊሳ ቤተሰቦች አይነተኛ መስካሪዎች ናቸው።

3 . የሼክ አብራሂም ቢሊሳ ማንነትና የእውቀት ምንጭ

የሼክ አብራሂም ቢሊሳ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት የተማሩ ሰዉ ሲሆኑ በአካባቢያቸው ማህበረሰብንም ሲያስተምሩ የነበሩ ብልጥ እና ብልህ ሰው እንደነበሩ አንዳንድ ሽማግሌዎች እና ቤተሰቦቻቸው ይናገራሉ ።

ሼህ ኢብራሂም ቢሊሳ በድሬዳዋ ከተማ በዋናነት በንግድ የተሰማሩ የነበሩ ሲሆን ጎን ለጎን በበጎ ስራና የተቸገረውን በመርዳት የሚታወቁ የነበሩ በተለይ ሰዎች እሳቸውን ፍለጋ ከምስራቅ እና ከምዕራብ ሀረርጌ ድረስ እየመጡ የተለያዩ ባህላዊ ህክምና ያክሙ እንደነበር ሽማግሌዎች ይናገራሉ በዚህ የተነሳ ከመንግስት አካላት በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመን በርካታ ጊዜ ጨና ተፈጥሮባቸው እንደነበረና እንደታሰሩም ጭምር ሽማግሌዎች ይናገራሉ ። እና እሳቸውም በ1990ዎቹ ህይወታቸው እንዳለፈም ይነገራል።

4. ቤታቸው በድሬደዋ በታሪክ ቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ስለመመዝገቡ

ይህ ታሪካዊ ቤት በከዚራ ድሮ አገልግሎት ይሰጥ ከነበረው መርሜይድ ክለብ ጎን ያለ ሲሆን ይህ ቤት በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን እና በድ/ዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት እንደ አንድ የድሬዳዋ ቅርስነት ተመዝግቦ የሚገኝ ቅርስ ነው።
Telegram channel https://t.me/ancient_history_oromoo