Get Mystery Box with random crypto!

ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮስ ሂፕ ሀፕ ኮምዩኒቲ ከተመሠረተ 4-5 ዓመታት ሆኖታል ሆኖም ግን በስ | Ethios Hip Hop Community ®

ሁላችንም እንደምናውቀው ኢትዮስ ሂፕ ሀፕ ኮምዩኒቲ ከተመሠረተ 4-5 ዓመታት ሆኖታል ሆኖም ግን በስራ ላይ የቆየበትን ዓመታት እና ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉት ግብዓቶች መኖራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት እኔ በግሌ ማሳካት ያለበትን ያህል አሳክቷል ብዬ አላስብም ረዘም ላለ ጊዜ በውጣውረድ ተጉዘናል ሁላችንም በአንድነት ሳይሆን ሁሉም ለየራሱ ይስራ እስኪመስል ድረስ መፈክራችን ሁሉም የየራሱን ነገር ነው የሚያሯሩጠው እንደዚህም አልነበረም ነገራቶች መሔድ የነበረባቸው ይህ በመሆኑም በኮምዩኒቲው ውስጥ በአርቲስቶች መካከል መከፋፈልን ፣ ትናንሽ ቡድኖች እንዲፈጠሩ ፣ለአንዳንዶች የስራ ተነሳሽነታቸው እንዲቀንስ ለሌሎችም ኮምዩኒቲውን ለቀው ለመውጣታቸው ምክንያት ሆኗል እኛም እንደ ኮምዩኒቲ ነገሮችን በተስተካከለ እና አግባብ ባለው መልኩ ባለመስራታችን ምክንያት ተስጥኦ ያላቸውን ሙዚቀኞች እያጣን ነው
ከላይ በጠቀስኳቸው እና ሌሎች በግልፅ በህዝብ ፊት ልናገራቸው በማልፈልጋቸው የግል ምክንያቶች ምክንያት ኮምዩኒቲው ለውጥ የሚያስፈልግበት ምርጫ አካሔዶ አዲስ አመራር የሚሾምበት ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ ዛሬ ላይ ቀደም ብዬ የኢትዮስ ሂፕ ሀፕ ኮምዩኒቲ መስራች እና የአሁን ሰዓት ፕሬዘዳንት የሆነው ካፖ እስራኤል ወይም Kapo da kapstone ጋር ደውዬ በስልክ ባወራሁት መሠረት ኮምዩኒቲው ምርጫ በማካሔዱ ሙሉ በሙሉ መስማማቱን ነግሮኛል ስለዚህ አዲስ ፕሬዘዳንት እና የስታፍ አባላትን ለመመረጥ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ምርጫ እናካሄዳለን
ሁሉንም የኢትዮስ ሂፕ ሀፕ ኮምዩኒቲ አባላት በዚህ ወሳኝ ሰዓት መጥታችሁ ድምፃችሁን እንድትሰጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ድምፃችሁ ያስፈልገናልና
ፕሬዘዳንት ሆኜ ኮምዪኒቲውን ለማስተዳደር ነኝ ብሎ ለሚያስብና መወዳደር ለሚፈልግ ማንኛውም ሠው ለመወዳደር
1) የኢትዮስ ሂፕ ሀፕ ኮምዩኒቲ አባል መሆን በኮምዩኒቲው ውስጥ ለ3 እና 4 ዓመታት የቆየ
2) ስለኮምዪኒቲው ታሪክ እና አሉ ስለሚባሉት ችግሮች በደንብ የሚያውቅ
3) ኮምዪኒቲው እንዴት መቀጠል አለበት ምን ምን ዕቅዶችስ አሉት ለኮምዩኒቲው የሚለውን ነገር የሚያስረዳ የታተመ ወረቀት በመያዝ ለሌሎች የኮምዩኒቲው አባላት በአካል በመገኘት ማቅረብ ይኖርበታል::

ምርጫው የሚካሄድበትን ትክክለኛ ቀን በቅርብ ቀን እናሳውቃቹሀለን እስከዚያው ደረስ ግን በቅርበት ተከታተሉን
የተለመደው ስብሰባችንን እና ምርጫውን የምናካሒድበት የምታውቁት ቦታ ካለ Comment ላይ ፃፉልን ይህንን ፅሁፍ ማየታችሁን እንዳውቅም #StickTogether ብላችሁ comment ላይ መፃፍም እንዳትረሱ

- 6 Dime$