🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​#ኢትዮጵ #የወረርሽኝ_ታሪክ_በኢትዮጵያ ታላቁ ረሀብ (1888_1892) የ19ኛው መቶ ክፍለ | ኢትዮጵ

​#ኢትዮጵ
#የወረርሽኝ_ታሪክ_በኢትዮጵያ
ታላቁ ረሀብ (1888_1892)

የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጨረሻው የኮሌራ ወረርሽኝ ታላቁን ረሀብ ታኮ የተቀሰቀሰ ነበር። በከባድ ረሀብ የተዳክመው ህዝብ ለማንኛውም ዓይነት በሽታ ተጋላጭ ስለነበር በቀላሉ ነበር የወረርሽኙ ሰለባ የሆነው። ወረርሽኙ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደተቀሰቀሰ ግልጥ ያለ መረጃ ባይኖርም በወቅቱ ምጽዋ የነበረው ጣሊያናዊው ሀኪም Filippo Rho ከሀጂ ጉዞ ከመካ በተመለሱ ሙስሊሞች አማካኝነት ሳይመጣ አልቀረም ሲል ግምቱን አስቀምጧል።

እንደ De Lauribar የታሪክ ዘገባ ወረርሽኙ በወቅቱ የጣሊያን ቅኝ ግዛት በነበረችው ኤርትራ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ተስፋፍቶ ነበር። በየመንገዱም ብዙ ሰው ይሞት ስለነበር የጣሊያን ወታደሮችና ካራቢኔሪዎች እየዞሩ ሬሳ በማቃጠል ስራ ላይ ተጠምደው እንደነበር ይነገራል። በወቅቱ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው ነበር። የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት በማሰብ። እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ ያስቸግረኛል።
ስለወረርሽኙ ክፋት የዓይን ምስክርነቱን የሰጠው የብሪቲሹ ተጓዥ Theodore Bent በ1893 ዓ.ም. የሰሜኑን ክፍል ከጎበኘ ብኋላ.......
“የእርስ በርስ ጦርነት፣ ረሀብ እና የኮሌራ ወረርሽኝ ከባድ ውድመት አድርሰዋል። ቀዪዎች ወናቸውን ቀርተዋል፣ የእርሻ መሬቶች አረም ወርሷቸዋል። በቦታው ተገኝቶ የሆነውን በዓይኑ ላልተመለከተ በሀገሪቱ ላይ ደርሶ የነበረውን አሰቃቂ ስቃይ እንዲህ ነው ብሎ ለመግለጽ ያስቸግረኛል። ለምሳሌ ደበርዋ በተባለች መንደር ሰው ሁሉ አልቆ ከድንጋይ ክምርና ከፈራረሰ ቤተክርስትያን በቀር ምንም አይታይም ነበር።”
..…ሲል በማስታወሻው አስፍሯል።
ደቡባዊው የኢትዮጵያ ክፍል
በ1892ዓ.ም. ኮሌራ በ ኤደን ባህረሰላጤ ተቀስቅሶ ብዙ ሰው አልቋል። እንደ ተጓዡ Drake Brockman ዘገባ በ ቡልሀር የነበረው ህዝብ ለወሬ ነጋሪም አልተረፈም ነበር። በዘይላ በበሽታው ከተጠቁ 369 ሰዎች 277 ሲሞቱ በበርበራ ደግሞ ከ 13 ታማሚዎች 11 እቺን ዓለም ተሰናብተዋል። በጅቡቲም እንዲሁ ብዙ ሰው ማለቁ ነው የሚነገረው።
በጅቡቲ ከሞቱት መካከል የቅኝ ግዛት አስተዳዳሪው Joseph Deloncle እና የወታደሮች ሀኪም የነበረው Dr. Aubrey ተጠቃሽ ናቸው።
ወደ መሀል ሀገር የተስፋፋው ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ካሉ የአምልኮ ማዕከላት አንዱ ከሆነው ድሬ ሼክ ሁሴን አናጂና መንደር ሲደርስ በወቅቱ ከነበረው ነዋሪ አራት አምስተኛውን አርግፏል። እንደ አጼ ምንሊክ ዜና መዋዕል ጸሀፊ ገብረሥላሴ ዘገባ በሀረር ከተማ ብዙ ሰው በወረርሽኙ ሲያልቅ ለተራበው ወገን ለመድረስ ከኦጋዴን ወደ መሀል ሀገር ከብቶች ሲነዱ የነበሩ ሰዎችም የበሽታው ሰለባ ሆነዋል።
ወረርሽኙ ንጉሱ ወዳለበት አንኮበር እንዳይደርስ እራሳቸውም በበሽታው ተጠቅተው የነበሩት አዛዥ ወልደ ጻድቅ ከብቶቹ በአዳል እንዲቆዩና መንገዶችም እንዲዘጉ አዘዙ። በወቅቱ ንጉሱ አጼ ምንሊክ ከአንኮበር ወረድ ብለው ዲቢ በተባለች ቦታ በጫካ ውስጥ ድንኳን ጥለው ይኖሩ ነበር።

20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
በዚህ ዘመን ዓለም ለኮሌራና ለሌሎች ብዙ በሽቶች መፍትሄ ማግኘት ጀመረች። የመጨረሻው ትልቁ የኮሌራ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በ1902ዓ.ም. ሲሆን ኢትዮጵያ የደረሰው በ1906ዓ.ም. ነበር። ይሁንና ወረርሽኙ በወሎ ብቻ ነበር ሪፖርት የተደረገው። ከዚህ ብኋላ የኮሌራ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ላይ በወረርሽኝ ደረጃ ጥቁር ጥላውን አላጠላባትም።
ታይፈስ፤ የወታደሩ በሽታ እንደ ቀደሙት ሁለቱ ወረርሽኞች እንደ ፈንጣጣና ኮሌራ የከፋ ባይሆንም ታይፈስ በኢትዮጵያ ተቀስቅሰው ጉዳት ካደረሱ ወረርሽኞች አንዱ ነው። በብዛት ወታደሩን ያጠቃ ስለነበር ታይፈስ የወታደር በሽታ በመባል ነበር የሚታወቀው።
ምንም እንኳን James Bruce በ1771 ዓ.ም. በጌምድር ሳለ የተመለከተውና የዘገበው በሽታ ታይፈስ ቢሆንም ታይፈስ እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ በስም አይታወቅም ነበር። ሌላው ይህን በሽታ የዘገበው Arnauld d’Abbadie እንደሚለው በጎንደር በ1842 ዓ.ም. የንዳድ ወረርሽኝ ተቀስቅሶ ነበር። በዛው ዘመን ከሴናር የሚመጡ ሲራራ ነጋዴዎች በዚሁ በሽታ ሲሞቱ በኢናሪያም በሽታው ተቀስቅሶ ነበር። ይሁንና ይሄ d’Abbadie ንዳድ ሲል የገለጸው በሽታ ታይፈስ ይሁን ሌላ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። ታይፈስ ለሚለው ቃል ትክክለኛ የአማርኛ ስያሜው ባይታወቅም Isenberg ንዳድ ብሎ ሲተረጉመው d’Abbadie መጋኛ ወይም በደዶ ሲል ይጠቅሰዋል።
ይህ ወጥ ያልሆነ የስም አጠቃቀስ የታይፈስን ታሪክ በኢትዮጵያ ለማጥናት አስቸጋሪ አድርጎታል።

አጼ ቴዎድሮስ
በንጽጽር በሚገባ የተጻፈው የታይፈስ ታሪክ በሰኔ ወር 1866ዓ.ም. በአጼ ቴዎድሮስ ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰው ነው። በዚህ ወቅት ንጉሱ በጣና ሀይቅ አቅራቢያ ቆራጣ በተባለች ስፍራ ሰፍረው ነበር። በቀን ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እያለቁባቸው የተቸገሩት አጼ ቴዎድሮስ ወደ በጌምድር በመውጣት ራሳቸውንና ሰራዊታቸውን ከሞት ታድገዋል።
ሌላው የታይፈስ ወረርሽኝ በ1870ዎቹ ኢትዮጵያን ለመውረር በሱዳን በኩል በመጡት የግብጽ ወታደሮች አማካኝነት የመጣው ነው። ነሀሴ 9 ቀን እንደተጻፈው እንደ ኮማንደሩ Rateb Pasha ዘገባ ከወታደሮቹ 160 ያክሉ በበሽታው ሲጠቁ በቀን ውስጥ ከ አራት እስከ ስድስት ወታደሮች ይሞቱበት ነበር። ወረርሽኙ ተስፋፍቶ በመስከረም 19 ቀን 384 የሱዳንና 76 አረብ ወታደሮች ማለቃቸውንም ኮማንደሩ ዘግቧል። ይህ ወረርሽኝ ብኋላ ወደ ነዋሪው የተሰራጨ ሲሆን ምን ያክል ሰው እንደተጎዳ ግን የተጻፈ ማስረጃ ሊገኝ አልቻለም።

ታላቁን ረሀብ ተከትሎ ብዙ የበሽታ ወረርሽኞች ተቀስቅሰዋል። በዚህ ወቅት ከተቀሰቀሱ ወረርሽኞች አንዱ ታይፈስ ሲሆን በወቅቱ የአጼ ምንሊክ አማካሪ የነበረው አልፍሬድ ኢልግ (Alfred ilg) እንደሚነግረን ታይፈስ፣ ተቅማጥና ፈንጣጣን የመሳሰሉት ወረርሽኞች ተባብረው በ1890 ዓ.ም. ከትግራይ ዘመቻ ወደ ሸዋ ሲመለስ ከነበረው የንጉሱ ሰራዊት 15% የሚሆነውን መንገድ አስቀርተዉታል። ከዚህም ሌላ ወደ ደቡብ የዘመተውን ወታደር አብዛኛውን የፈጀው የታይፈስ ወረርሽኝ እንደነበር ይነገራል። በተለይም ወደ ከፋ የዘመተው በራስ ወልደ ጊዮርጊስ የተመራው ጦር በዚህ ወረርሽኝ እጅጉን መጎዳቱንና ወታደሮቹም ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ወረርሽኙን ይዘው እንደመጡ Carlo Annoratone እና Lincoln de Castro የተባሉ የህክምና ባለሞያዎች በጻፉት የታሪክ ማስታወሻ ጠቅሰዋል።
(ይቀጥላል)
[በቀጣይ በመጨረሻው ክፍልና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የወረርሽኝ ታሪክ በኢትዮጵያ እንገናኛለን።]
ምስል - ታላቁ ረሃብ
ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።