Get Mystery Box with random crypto!

የ2013 የኢትዮጵያ ውሹ ሻምፒዮና ውድድር በአዲስ አበባ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ፡፡ ሚያዚያ | Ethiopia Wushu Federation

የ2013 የኢትዮጵያ ውሹ ሻምፒዮና ውድድር በአዲስ አበባ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ፡፡
ሚያዚያ 14 / 2013 ዓ/ም
ከሚያዚያ 11 – 14 / 2013 ዓ/ም በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የ2013 ዓ/ም የኢትዮጵያ ውሹ ሻምፒዮና ውድድር በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል ፡፡
ውድድሩ የኮቪድ ፕሮቶኮል መሰረት በማድረግ በሁለቱም ፆታ የተካሄደ ሲሆን በተደረገው ውድድር ፦
በሁለቱም ፆታ በሳንሹና በታኦሎ አዲስ አበባ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል ፡፡
በአርትና በነጻ ፍልሚያ ውድድር ሳንሹ በሴቶች ፦ ፅዮን ቢንያም ከአዲስ አበባ
ታኦሎ በሴቶች ፦ ረቂቅ ንጉሴ ከአዲስ አበባ
ሳንሹ በወንዶች ፦ ወርቅነህ መኮንን ከአዲስ አበባ
ታኦሎ በወንዶች ፦ ዮሐንስ አዱኛ ከኦሮሚያ ኮከብ ተጨዋች በመሆን የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በተጨማሪም ኦሮሚያ ክልል የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ፡፡
በሻምፒዮና ውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ ኦሮሚያ ክልል ፣ ሐረሪ ክልልና አፋር ክልል ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡