Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ውሹ ፌዴሬሽን ከህዳር 22-26/2014. ዓ.ም ድረስ ደማቅ የሆነ ከቀደመው ጊዜ የተሻለ | Ethiopia Wushu Federation

የኢትዮጵያ ውሹ ፌዴሬሽን ከህዳር 22-26/2014. ዓ.ም ድረስ ደማቅ የሆነ ከቀደመው ጊዜ የተሻለ እና አሪፍ የሚባል ሽልማትን የሚያስገኝ ለሁሉም ክፍት የሆነ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ 4ኪሎ ስ/ት/ስ/ማዕከል ያካሂዳል። ውድድሩ በአርት 16 አመት እና ከዛ በላይ እንዲሁም በፋይት 18 እና ከዛ በላይ የሆናቸው ሁሉ መሳተፍ ይችላሉ ።
የውድድሩ ካታጎሪ እንደሚከተለው ይሆናል።
*በአርት ሴት - ናንኳን/ሰርድ ጀነሬሽን/
- ቻንኳን /ሰርድ ጀነሬሽን/
*በአርት ወንድ - ናንኳን/ሰርድ ጀነሬሽን/
- ከጀል/ሰርድ ጀነሬሽን/
- ብሮድ /ሰርድ ጀነሬሽን/
በሳንሹ/ፋይት/ ደግሞ..በሴት- 48/52 ኪሎ
- 53/56 ኪሎ

በሳንሹ/ፋይት/ደግሞ.በወንድ-48/52 ኪሎ
- 53/56 ኪሎ
- 57/60 ኪሎ
- 61/65 ኪሎ
- 66/70 ኪሎ ናቸው......
ማሳሰቢያ ----ለእያንዳንዳቸው የውድድር ካታጎሪ ለመመዝገቢያ 1000/አንድ ሺህ ብር/ ሲሆን በአርትም በፋይት ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ----- ወርቅ ላመጣ 10 ሺህ
ብር ላመጣ 7ሺ
እንዲሁም ነሀስ ላመጣ 5ሺ ብር ሽልማት ያለው መሆኑንም መግለፅ እንወዳለን። በተጨማሪም በፋይት ውድድሩ ላይ በዉሹ ህግ የሚዳኙ ተወዳዳሪዎች ሁሉ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑንእያሳወቅን.....መመዝገቢያውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000097583149 የኢ/ያ ዉሹ ፌዴሬሽን ብላችሁ በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ። የምዝገባው ጊዜ እስከ ህዳር 18/2014 ድረስ ሲሆን ለበለጠ መረጃ 0911673538/0913618715 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ።የኢትዮጵያ ዉሹ ፌደሬሽን