🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አደዋ በጂጂ የሰው ልጅ ክቡር ሰው መሆን ክቡር ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር በደግ | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

አደዋ በጂጂ

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል ሰው ሊኖር ሰው ሰው ሞቶ
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆሙኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር በድል እኖራለሁ
ያው በቀን በቀን በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ …. አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ ሄ......ተናገሪ ተናገሪ
የድል ታሪክሽኝ አውሪ
ሄ.....ይ....ተናገሪ......ሄ.........ይ