🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

………ከላይየቀጠለ የዓድዋ ድል በዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ድብዳቤዎች ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ የዓድዋን | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

………ከላይየቀጠለ

የዓድዋ ድል በዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ድብዳቤዎች

ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ የዓድዋን ድል አስመልክተው ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን የዛሬ 124 ዓመት የጻፉለት
የምሥራች ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር

“የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት
ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ››አጤ ምኒሊክ በመጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም.

ለፈረንሳዊው ሙሴ ሸፍኔ በላኩለት ደብዳቤ ያቸው እንዲህ ብለዋል

‹‹… ከአላጌ ጦርነት በኋላ፣ ጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር፣ የክርስቲያንም ደም በከንቱ አይፍሰስ፣ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግ ተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም፡፡ ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን…፡፡››

በማለት ያስታወቁ ሲሆን ምኒልክ ለሞስኮብ ንጉሥ ኒቆላዎስም መጋቢት 23 ቀን 1988 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤያቸውም

‹‹እንደ አውሮፓ ነገሥታት ሥራት
ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቀኝ፣ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ጀመረ፡፡ ጥንት ከአህዛብና ከአረመኔ አገራችን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረግሁት…›› ብለው መጻፋቸው ይጠቀሳል ፡፡

አልፋና ኦሜጋ የማይረሳው መስዋዕትነት !
አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራል !

ልክ የዛሬ 124 ኛ አመት እሁድ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓም ታላቁ የዓድዋ ድል በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ ተበሰረ !

ይህ የጥቁር ህዝብ በቅኝ ገዥዎች ከተቀዳጃቸው የዓድዋ ድል እውን እንዲሆን
አቀበት የወጡ ፣
ቁልቁለት የወረዱ ፣
እርጥብ የጨሰባቸው ፣
ደረቅ የነደደባቸው ፣
ከቤታ ቸው የተፈናቀሉ ፣
የቆሰሉ ፣
የሞቱ ፣
መዳረሻቸው የጠፋ ጀግኖቻችን አልፋና ኦሜጋ የማይረሳው መስዋዕትነት ነው።

ይህ አንጸባራቂ ድልም እነሆ አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራል !
የዛሬ 124 ዓመት ከዘመነው የፋሽሽት ጣሊያን ጦር እና ጦር ሰራዊት በላይ የጥቁር ህዝብ ብሔራዊ ክብርና ኩራት ልቀው የታዩበት የጦርነት አውድማ ነው !

ዓድዋ

ምንጮች :
* በታዋቂ የታሪክ አዋቂዎች ከተጻፉት የታሪክ መዛግብት፣
*ከአድዋው ጦርነት ዙሪያ ከቀረቡት የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ፣
* ልዩልዩ

***
ሀገርን ከነድንበሩ፣
ታሪክን ከነባህሉ፣
ቋንቋን ከነፊደሉ ያቆዩልን፣
ለዛሬው ማንነታችን የአካል እና የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉልን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን እና አርበኞቻችንን እናመሰግናለን!
#ክብር_እነሱ_ወድቀው_ኢትዮጵያን_ከእነሙሉ_ክብሯ_ላስረከቡን_አርበኞቻችን_

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_125
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@yetarikdersan