Get Mystery Box with random crypto!

#አእምሮ_አለህ? በአንድ ነገር ላይ ፍፁም ኃይል አለህ ያም- ሀሳብህ ነው፡፡ ይህ ለሰው ልጅ ከታ | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

#አእምሮ_አለህ?

በአንድ ነገር ላይ ፍፁም ኃይል አለህ ያም- ሀሳብህ ነው፡፡ ይህ ለሰው ልጅ ከታወቁት እውነታዎች ሁሉ እጅግ ጠቀሚው እና አበረታቹ ነው፡፡ የሰውን አምላካዊ ተፈጥሮ ይገልፃል፡፡ ይህ አምላካዊ ስልጣን የራስህን እጣ ፈንታ የምትወስንበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ የራስህን አእምሮ መቆጣጠር ካልቻልክ፥ ሌላ ምንም ነገር እንደማትቆጣጠር እርግጠኛ ትሆናለህ፡፡ በሀብቶችህ ግድየለሽ መሆን ካለብህ፥ ቁሳዊ ነገሮች በሆኑት ላይ ይሁን፡፡ አእምሮህ መንፈሳዊ ሀብትህ ነው፡፡ አምላካዊ ስልጣን ስለ ተሰጠህ በጥንቃቄ ጠብቀህ ተጠቀምበት፡፡ ለዚህ አላማ ራስህን የመግዛት ኃይል ተሰጥቶሃል፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሌሎችን አእምሮዎች በአሉታዊ ሀሳቦች ከሚመርዙ ሰዎች የሚጠብቅ የሕግ ከለላ የለም፡፡ ይህ የጥፋት ዓይነት ከባድ ህጋዊ ቅጣቶች የሚያስቀጣ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ በህግ የተጠበቁትን ቁሳዊ ነገሮች የማግኘት ዕድሎችን ያጠፋል፡፡ አሉታዊ አእምሮዎች ያሏቸው ሰዎች የሰውን ድምፅ የሚቀዳ እና የሚያበዛ መሳሪያ መስራት እንደማይቻል ቶማስ ኤድሰንን ለማሳመን ሞክረዋል፡፡ “ምክንያቱም” አሉ “እንደዚህ ያለ መሳሪያ የሰራ አንድም ሰው የለም፡፡” ኤድሰን ግን አላመናቸውም፡፡

አእምሮ ያሰበውን እና ያመነውን ማንኛውንም ነገር አእምሮ መስራት እንደሚችል አውቋል፡፡ ያ እውቀት ነው ታላቁ ኤድሰንን ከህዝብ መንጋ በላይ ያደረገው፡፡

ኤፍ. ደብልዩ. ውልወርዝ በአምስት እና በአስር ሳንቲም ትርፍ ንግድ ለመጀመር ሲሞክር አሉታዊ አእምሮዎች ያላቸው ሰዎች እንደሚከስር ነግረውታል፡፡ አላመናቸውም፡፡ በተግባር ዕቅዶቹን ከእምነት ጋር ካጣመረ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደሚችል አውቋል፡፡ የሌሎች ሰዎችን አሉታዊ ሀሳቦች ከአእምሮው አውጥቶ የራሱን ትክክለኛ ተግባር በመስራት ከመቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት አከማችቷል፡፡

ሄነሪ ፎርድ የመጀመሪያውን ጥሩ ሆና ያልተሰራች አውቶሞቢሉን በዳትሮይድ መንገዶች ሲሞክር ተጠራጣሪ ቶማሶች ማረጋገጫ ካላዩ የማያምኑ ሰዎች በመጠቋቆም አፊዘውበታል፡፡ አንዳንዶች ይህ ነገር ተግባራዊ አይሆንም አሉ፡፡ ሌሎች እንደዚህ ያለ ለአያያዝ ለማይመች መሳሪያ አንድም ሰው ገንዘብ አይከፍልም አሉ፡፡ ፎርድ “በአስተማማኝ የሞተር መኪኖች ምድርን እሞላታለሁ” አለ፡፡ አደረገውም፡፡

ብዙ ሀብትን የምትፈልግ ከሆነ አንድ ነገር አስታውስ - በሄነሪ ፎርድ እና በቀጠራቸው መቶ ሺ ሰራተኞች መሃል ያለው ልዩነት ምን ነበር? ፎርድ አእምሮ ነበረው፤ አእምሮውንም ተቆጣጥሮታል፤ ሌሎችም ሰራተኞች አእምሮ ነበራቸው ሆኖም አልተቆጣጠሩትም።

#አስበህ_ሀብታም_ሁን መጽሐፍ