Get Mystery Box with random crypto!

ገራዶ ሚዲያ

Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Logo of telegram channel geradomedia — ገራዶ ሚዲያ
Channel address: @geradomedia
Categories: News
Language: English
Subscribers: 679
Description from channel

🔸ሁሉን አቀፍ የመረጃ ምንጭ!🔸
✍ ፃፉልን @geradomediabot
fb.com/geradomedia
twitter.com/geradomedia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages

2021-05-07 09:14:35
"ኢትዮጵያን ሰፋ አድርገን እናስባት! ለሁላችንም በቂ ነች! 'የፉክክር ቤት ሳይዘጋ አደረ' አይነት እንዳንሆን!"
.
መልካም ቀን

t.me/geradomedia
735 views....., 06:14
Open / Comment
2021-05-06 21:47:08
#በርበራ_ወደብ

ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን በጋራ ለመጠቀም ስምምነት ፈረሙ። ስምምነቱ በኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ትንሳኤ ማግስት ይፋ መደረጉን ተከትሎ መሆኑ አንድምታውን ከፍ ያደርገዋል።

[እስሌማን አባይ]

t.me/geradomedia
1.2K views....., 18:47
Open / Comment
2021-05-06 21:47:02 ገራዶ ሚዲያ pinned a photo
18:47
Open / Comment
2021-05-06 21:46:57
ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ

- እዚህ ቻናል ላይ ምርትና አገልግሎታችሁን ማስተዋወቅ የምትፈልጉ @geradomediabot ወይም @gashaw02 ላይ አናግሩን!

ለ 24 ሰዓት (2 ልጥፍ) ..... 50 ብር
ለ 1 ሳምንት (7 ልጥፍ) ... 240 ብር
ለ 1 ወር (15 ልጥፍ ... 450 ብር
ለ 1 ወር (20 ልጥፍ) ... 550 ብር
ለ 1 ወር (30 ልጥፍ) ... 800 ብር በመክፈል ማሰራት ትችላላችሁ።
1.2K views....., 18:46
Open / Comment
2021-05-06 20:30:20
#Update ተመድ ለኢትዮጵያ 65 ሚሊየን ዶላር ለቀቀ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰብአዊ እርዳታዎች የሚሆን 65 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ መልቀቁ ታውቋል። ከ65 ሚሊዮን ዶላሩ ውስጥ 40 ሚሊዮን ዶላሩ በትግራይ ክልል ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል ሲሆን፥ ቀሪው ደግሞ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ይውላል ተብሏል፡፡

t.me/geradomedia
943 views....., edited  17:30
Open / Comment
2021-05-06 17:57:47
ፋሲል ከነማ ሻምፒዮን ሆኗል!

ፋሲል ከነማ በ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ገና 4 ጨዋታዎች እየቀሩት ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ፋሲል ከተማ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ዛሬ ባካሄዱት ጨዋታ አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ ነው።

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

t.me/geradomedia
2.1K views....., 14:57
Open / Comment
2021-05-06 17:39:56
የአቶ አበረ አዳሙ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ!

የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርአት በባህርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን መፈፀሙን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

t.me/geradomedia
2.1K views....., edited  14:39
Open / Comment
2021-05-06 13:13:53
ሸኔ ማን ነው??

በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይደመጣሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ የፌዴራል ጠ/አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው? 

"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው። እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን።

ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ ህወሓት ተመዝግቦ፣ ህጋዊ እውቅና፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም፤ ስለዚህ ስያሜው እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት 'ኦነግ ሸኔ' ወይም 'ሸኔ' ከሚባለው 'ሸኔ' የሚለውን መርጠናል።

እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል።

አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም።

በተለምዶ በሁለት መንገድ ይጠራ ነበር፤ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር፥ በአጭሩ 'ሸኔ'ም ይባላል፤ 'ኦነግ ሸኔ' የሚባለውን አጠራር 'ኦነግ' የሚባል በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት አለ ስለዚህ ከሱ ጋር ማምታት ሊፈጥር ይችላል ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራባቸው ስያሜዎች 'ሸኔ' የሚለው ብዙ ሰው ስለሚያውቀው በዛ እንዲሰየም ተመርጧል" ብለዋል። #Tikvah

t.me/geradomedia
1.2K viewsGashu, 10:13
Open / Comment
2021-05-06 12:32:14
አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ተወያዩ!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ሲሪ ራማፎዛ ጋር ፕሪቶሪያ ተገናኝተው በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያ ያሉትን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል። የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ወገን ድርድር እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ያላትን ፅኑ አቋም አስረድተዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ወደ ኒጀር ያቀኑ ሲሆን ለኒጀር ፕሬዘዳንት መሀመድ ባዙም ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ መሪዎቹ ባደረጉት ውይይት የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት አስረድተዋል። #AMN

t.me/geradomedia
32 viewsGashu, 09:32
Open / Comment
2021-05-06 10:15:49
#Update

“ህወሓት” እና “ሸኔ” ን በሽብርተኝነት ተፈረጁ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ በሚንስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፅድቆ "ህወሓት” እና “ሸኔ” ን በሽብርተኝነት ፈርጇል። #EBC

t.me/geradomedia
316 viewsGashu, edited  07:15
Open / Comment