Get Mystery Box with random crypto!

#የጠቅላይ_ሚኒስትሩ_ጥሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ | ገራዶ ሚዲያ

#የጠቅላይ_ሚኒስትሩ_ጥሪ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ አቅርበዋል። መልዕክቱም እንደሚከተለው ቀርቧል።

"የእናት ሆድ ዥንጉርጉርነት የልጆችዋን መልክና ጠባይ አንድ አይነት እንደማያደርገው ሁሉ፤ ከኢትዮጵያ ማህጸን በቅለው፣ የክብር ቦታ አግኝተውና ከሩብ ክፍለ ዘመን ለተሻገረ ጊዜ ሀገር የአስተዳደሩ ሰዎች መልሰው ሀገራችንን ከጀርባ ቢወጓት፥ የእናትን ውርደት በማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ርብርብ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

ዳሩ ግን፥ ዛሬም የጁንታው ሞት ያልተዋጠላቸው ከዥንጉርጉር ማህጸኗ የፈለቁ ሰዎች ከሀገራችን ጠላቶች ጋር እያበሩ፣ የተዛቡ መረጃዎች መርጨቱን የዕለት እንጀራቸው አድርገውታል። እንዳሻቸው መሆን ካልቻሉ ኢትዮጵያ እንድትኖር አይፈልጉም። በሕግ ማስከበር ዘመቻው ያጡትን ድል በወሬ ግንባር ለመመለስ ተንኮልን መሣሪያ፣ ሐሰትን ጥይት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

በመሆኑም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች፥ ስለ ሀገራችሁና ስለ ወቅታዊው ጉዳይ ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በመናገር፤ የሀገራችንን መልካም ክብርና ስም ለማጥፋት የተነሱ ሰዎችን ድል በመንሳት፤ ሐሰትን በእውነት እንድታሸንፉ ጥሪ አቀርባለሁ።"

t.me/geradomedia