🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የማይካድራው ጭፍጨፋ ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ! ህወሓት አደራጅቶታል በተባለው እ | ገራዶ ሚዲያ

የማይካድራው ጭፍጨፋ ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ!

ህወሓት አደራጅቶታል በተባለው እና “ሳምሪ” በተሰኘው ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን በማይካድራ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን የተገደሉበት ዓለም አቀፍ የሽብር ወንጀል ሆኖ ተመዘገበ፡፡ ወንጀሉ የተመዘገበው በዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሳለፍነው ህዳር ወር የተፈጸሙ የሽብር ወንጀሎችን ዝርዝር ያወጣው ተቋሙ የማይካድራው ጭፍጨፋ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው ሲል አስቀምጧል፡፡ ጭፍጨፋው በመላው ዓለም ከተፈጸሙ 10 ተመሳሳይ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚው ነው ያለም ሲሆን ቦኮሀራም በተጠቀሰው ወር በናይጄሪያ ከፈፀመው የሽብር ወንጀል እንደሚበልጥ ነው የገለጸው፡፡

የተቋሙ የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ጭፍጨፋው ማንነትን መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ነው ማለቱንም ነው ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ ዳይሬክቶሬቱ 600 ንጹሃን መጨፍጨፋቸውንም ይፋ አድርጓል፡፡

ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በማይካድራ እና በአካባቢው የተፈጸመው ጭፍጨፋ በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር አስተባባሪነት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ጭፍጨፋው በጦር ወንጀለኝነት ጭምር ሊያስጠይቅ የሚችል “የግፍና ጭካኔ ወንጀል” ነው ያለ ሲሆን ከ600 የሚልቁ ንጹሃን መገደላቸውን ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡ #AlAin

t.me/geradomedia