🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#የዩኤኢ_ኤምባሲ_ላይ_ጥቃት....... ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ | ገራዶ ሚዲያ

#የዩኤኢ_ኤምባሲ_ላይ_ጥቃት.......

ከውጭ የሽብር ቡድን አባላት ተልእኮ በመቀበል አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (ዩኤኢ) ኤምባሲ ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ እንዲሁም የአፍሪካና የዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን የአዲስ አበባን በጎ ገጽታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ የነበሩት ቡድኖችን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት 15 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣አሸባሪዎች ለጥቃት ሊጠቀሙባቸው ያዘጋጇቸው ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎች እና ለፍንዳታ ሥራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ከኅዳር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ መረጃ ተቋማት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል እና የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የታቀደውን የሽብር ጥቃት ማክሸፍ ችሏል።

የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት መካከል የቡድኑን አባላት ሲመራ የነበረው የ35 ዓመቱ ዓሊ አህመድ አርዳይቶ ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ለዓሊ አህመድ አርዳይቶ ለሽብር ጥቃቱ ማቀነባበሪያነት እንዲውል በዐሥር ሺዎች የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር እንደተላከለት ከተሰበሰቡ መረጃዎች ማረጋገጥ እንደተቻለ ተጠቁሟል።

ከዚህ ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበረው እና የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህቡዕ ሲያሴር የቆየው መሐሙድ አብዱልቃኒ የተባለ ሌላ ተጠርጣሪም ከቀናት በኋላ በቁጥጥር ሥር በዋለበት ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የጦር መሣሪያዎች፣ ለፍንዳት ስራ የሚውሉ ተቀጣጣይ ቄሳቀሶች እና ሰነዶች መያዛቸውን አስታውቋል።

ሌላ ተመሳሳይ ተልእኮ የተሰጠው ቡድን በሱዳን ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ላይ ተመሳሳይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ መሪ ከውጭ አመራር የሚሰጠው ኑሮውን በስዊዲን ያደረገው አህመድ እስማኤል የተባለ ግለሰብ ነው።

የሽብር ጥቃት ዕቅድ በማውጣት እና ከሽብር ቡድኑ አባላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኤምባሲ የደህንነት መረጃዎች እንዲሰበሰቡ አቅጣጫ ሲሰጥ ቆይቷል።

ከአውሮፓ፣ አፍሪካ እና እስያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ጋር የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እና ብርቱ ክትትል በማድረግ አህመድ እስማኤል በስዊዲን ሀገር በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

t.me/geradomedia