Get Mystery Box with random crypto!

ወደ መቐለ ተልኮ መደረሻው ሳይታወቅ የቆየው 1.3 ቢሊየን አዲሱ ብር ተገኘ! በምርጫ ቦርድ ተዘር | ገራዶ ሚዲያ

ወደ መቐለ ተልኮ መደረሻው ሳይታወቅ የቆየው 1.3 ቢሊየን አዲሱ ብር ተገኘ!

በምርጫ ቦርድ ተዘርዞ ህልውናው እንዲከስም የተደረገው ቀድሞ የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሃት) እና በማዕከላዊው መንግስት መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰ ዕለት ጥቅምት 24 ቀን 2013 አ.ም ምሽት ወደ ትግራይ መቐለ በአሮጌው ብር እንዲቀየር በብሄራዊ ባንክ በአውሮፕላን የተላከው አዲሱ 1.3 ቢሊየን ብር መዳረሻው መታወቁን ዋዜማ ራዲዮ ሰምቻለሁ ብላለች።

በአሮጌው ብር እንዲቀየር የተላከው 1.3 ቢሊየን ብር መቐለ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ክፍል ውስጥ ነው ታሽጎ የተገኘው።

ህወሃት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈፅሟል በተባለበትና ግጭቱ ወደለየለት ጦርነት በተሸጋገረበት በዚያ ዕለት አሮጌውን የብር ኖት እንዲተካ የተላከው ብር መዳረሻ አልታወቀም ነበር።

በወቅቱም መንግስት ገንዘቡን በትግራይ ክልል ላሉ የተለያዩ ባንኮች አከፋፍያለሁ ብሎ በብሄራዊው የቴሌቭዥን ጣብያ ማስነገሩ ይታወሳል። ማይጨው፣ አደዋ፣ ሽሬ እንዳስላሴ እና አዲግራት ላሉ የተለያዩ ንግድ ባንኮች ብሩ ተከፋፍሏል ተብሎም ነበር። ሆኖም በወቅቱ በክልሉ ከነበረው ሁኔታ አንጻርና እንደተባለውም ብሩ በክልሉ ላሉ የባንክ ቅርንጫፎች እንዳልተከፋፈለ ዋዜማ ራዲዮ ዘግባ ነበር።

የ1.3 ቢሊየን አዲሱን ብር እጣ ፈንታም የፌዴራል መንግስት የመቐለ ከተማን ከተቆጣጠረም በኋላ በመቐለ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ አዲስ ስራ እንኪጀምር እንዳላወቀ ተሰምቷል። ሰሞኑን በመቐለ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እንደገና ስራ ሲጀምር ግን የቅርንጫፉ ሰራተኞች ብሩን በአንድ ክፍል ታሽጎ ማግኘታቸውን ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቼ መረጃ አግኝቻለሁ ብላ ዘግባለች።

t.me/geradomedia