Get Mystery Box with random crypto!

'ሰልፎቹን አስመልክቶ ከአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበውን ቅሬታ ቦርዱ በሚዛኑ ማየት አለበት' | ገራዶ ሚዲያ

"ሰልፎቹን አስመልክቶ ከአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበውን ቅሬታ ቦርዱ በሚዛኑ ማየት አለበት" - አቶ ፍቃዱ ተሰማ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች በተካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች "በህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ተመዝግበን እያለን ስማችን ጠፍቷል" በሚል አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ቅሬታ ተመስርቶ ያስተላለፈው ውሳኔ በሚዛናዊነት መታየት አለበት የሚል አቋም እንዳላቸው የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ፡፡

ሃላፊው ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የክልሉ ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለብልጽግና ፖርቲ ያለውን ድጋፍና ክብር አሳይቷል ብለዋል፡፡ ህዝብ የተሰማውን ለምን በእዚህ ደረጃ ተነሳስቶና ፈንቅሎ ወጣ? የሚለው መታየት አለበት፣ ትችቱን ያነሱ ወንድሞቻችንም በእኛ በኩል ምን ጉድለት አለ? ብለው ራሳቸውን ማየት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡

ህዝቡ በራሱ የቀሰቀሰውና የጣው ሰልፍ እንደመሆኑ መወቀስ ያለበት ያስተላለፈው መልእክት ብቻ ሳይሆን እነዚህ አካላትስ በተለያየ ጊዜ ምን ሲያደርጉ እንደነበር ብሎ ቦርዱ መጠየቅ ነበረበት ብለዋል አቶ ፈቃዱ፡፡

ህዝብን እንደህዝብ የሚያንኳስሱ፣ የሚያጋጩ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ፣ የጁንታው ተላላኪ በመሆን የሚሰሩ አካላት ህዝቡም ያውቃል እነርሱም ያውቃሉ ብለን እንገምታለን ተጨባጭ ማሳያዎችም አሉ ብለዋል፡፡

ምርጫ ቦርድን እናከብራለን፣ ህጉንም ከማንም በላይ እናከብራለን ኢትዮጵያ ጠንካራ ገለልተኛ ተቋም እንዲኖራት ከማንም በላይ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ ለእዚህም እንሰራለን፣ እንታገላለን፣ እንረባረባለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ (ኢ ፕ ድ)

t.me/geradomedia