🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በትግራይ ቀውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስጋትና ጥያቄ.... የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር | ገራዶ ሚዲያ

በትግራይ ቀውስ የዩናይትድ ስቴትስ ስጋትና ጥያቄ....

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ክልል ባለው ቀውስ ስጋት እንዳደረባቸው ገልፀው ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ያልተገደበ የሰብኣዊ እርዳታ ሊደረግ ይገባል አሉ፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ የተወያዩት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እና ሊካሄድ የታሰበው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን ዐቀፍ ለውጥ ለመደገፍ ላሳየችው ተነሳሽነት ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

በሌላ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ ‹‹በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ፤ የሰብኣዊ መብት ጥሰትንም እየፈፀሙ ነው›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋን በኤርታር የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አሳውቋል፡፡

በክልሉ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት፣ ዘረፋ በስደተኛ ካምፖች ላይ ጥቃት እና ሌሎችም የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል ተጣርተው ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ሰዎች ሕግ ፊት እንዲቀርቡ መጠየቄን እቀጥላለሁም ነው ያለችው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ምርመራውን በራሴ አቅም አከናውናለሁ የሚል አቋም ነው ያለው፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ አለ የሚለውን ሪፖርት እንደማይቀበሉት ሲገልፁ ከርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ወደ አስመራ ‹‹ሮኬት ሲተኮስብት የነበረ ኃይል ወደ ድንበር አይጠጋም ማለት አይቻልም›› ከሚል ምላሽ በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ ሉኣላዊ ግዛት የሆነችው ትግራይ ገብቷል የሚል መረጃን አይቀበለም፡፡

(አሐዱ ቴሌቪዥን)

t.me/geradomedia