🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የአፍሪካ ኅብረትና የጆ ባይደን አስተዳዳር....? የአሜሪካው አድስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳ | ገራዶ ሚዲያ

የአፍሪካ ኅብረትና የጆ ባይደን አስተዳዳር....?

የአሜሪካው አድስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳዳር ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ጠንካራ ትስስርን እንደገና ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ገለፃ ካደረጉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያለውን ትስስር እንደገና እንደሚገነቡት ቃል ገብተዋል፡፡

ቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ ከ2 ዓማት በፊት ‹‹አፍሪካዊያንን የማይረቡ አገራት ያሉበት አኅጉር›› ሲሉ መግለፃቸው ቁጣን ቀስቅሶ እንደነበርና ኅብረቱን ከዩናይትድ ስቴትስ ማራራቁ ይታወቃል፡፡

ምንም እንኳን ትራምፕ ‹‹እኔ ዘረኛ አይደለሁም›› ሲሉ ሊያስተባብሉ ቢሞክሩም በተግባር ግን ለጥቁር ቆዳ ቀለም ሕዝቦች ያላቸው ጥላቻ በተለያየ ጊዜ ሲገለጥ ኖሯል፡፡

ነጩን ቤተ መንግሥት የተረከቡት ባይደን ግን ከኅብረቱ ጋር የነበረውን ጠንካራ ትስስር እንደሚመልሱት ነው የገለፁት፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኅብረቱ በአኅጉሪቱ ያሉ ግጭቶችን በመፍታት ጠንካራ እንዲሆን እገዛ እንደሚያደርጉ ነው ያሳወቁት፡፡

ዩናይትድ ስቴትስና አፍሪካ በባራክ ኦባማ ዘመንም ጠንካራ ትስስር ነበራቸው፡፡ (AhaduTV)

t.me/geradomedia