Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የተመረቀው ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ.... የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓር | ገራዶ ሚዲያ

ዛሬ የተመረቀው ቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ....

የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፌደራል ደረጃ ከተመረጡ አራት ሞዴል አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አንዱ በመሆን ጥር 25/2009 የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።

በ2010 ነበር ለመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሥራ ውል ተሰጥቶ ወደ ግንባታ ተገብቷል።

የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ በ260 ነጥብ 35 ሄክታር መሬት ላይ ነበር በ2010 የተጀመረው። በአጠቃላይ ፓርኩ በ1 ሽህ ሄክታር ላይ ይለማል።

ለቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ 7 መጋቢ የገጠር የሽግግር ማዕከላት አሉት። ማዕከላቱም ሞጣ፣ አማኑኤል፣ ፍኖተሰላም፣ ዳንግላ፣ መርዓዊ፣ እንጅባራ እና ቻግኒ ይገኛሉ።

የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ትምህርት ቤትን፣ የህፃናት ማቆያን፣ ክሊኒክን፣ መኖሪያ ህንፃና ሌሎችም ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ይገኙበታል።

ፓርኩ በዋናነት የሚያካትታቸው ኢንዱስትሪ አይነቶች የግብርና ምርትን በግብዓትነት የሚጠቀሙና የሚያቀነባብሩ፣ ምርታቸውን በጋራ ወይም በተናጠል ወደ ውጭ የሚልኩ፣ ለግብርናው ምርት መዘመን መሰረት የሚሆኑ፣ የተሻሻለ ቴክኖሎጅ የሚያስተዋውቁ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽኦ ያላቸውና ሌሎችም ይገኙበታል።

የምግብ መጠጥና ፋርማሲቲዮካል፣ የጥራጥሬና ቅባት እህል ውጤቶች ማቀነባባሪያ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ፣ የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎችም በፓርኩ እንዲለሙ የተፈቀዱ የኢንዱስትሪ ዓይነቶች ናቸው።

ፓርኩ ደረጃውን የጠበቀ 13 ኪ.ሜ ኮንክሪት አስፓልት መንገድ፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ ማከሚያና ማከማቻ፣ መካከለኛና አነስተኛ የመብራት መስመር ግንባታ፣ የቴሌ-ኮም መስመር፣ የመረጃ ማዕከል፣ የገበያ ማዕከል፣ የስልጠና ማዕከል፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ማዕከል፣ የፖሊስ ጣቢያ፣ የጉምሩክና ጥበቃ ማዕከል፣ ሞዴል የኢንዱስትሪ ሸዶች፣ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች አካቷል።

ምንጭ፦ የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

t.me/geradomedia