🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ኦነግ በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚያስመዘግበው እጩ ተወዳዳሪ እንደሌለው አስታወቀ! በአቶ ዳውድ ኢብሳ | ገራዶ ሚዲያ

ኦነግ በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሚያስመዘግበው እጩ ተወዳዳሪ እንደሌለው አስታወቀ!

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጪው አገር አቀፍ ምርጫ የሚያስመዘግው እጩ እንደሌለው አሳውቋል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዘገበው ፓርቲው በየምርጫ ክልሎች ላስመዘግብ ያሰብኳቸው እጩ ተወዳዳሪዎቼ በሙሉ በእስር ላይ ስለሚገኙ ነው የማስመዘግበው የለኝም ያለው፡፡ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ በቴ ኡርጌሳ እንዳሉት ኦነግ አስፈላጊ የሚባሉ የምርጫ ዝግጅቶችን ተንቀሳቅሶ ማከናወን አልቻለም፡፡

በአሁኑ ወቅት በአመራሮቹ መካከል አለመግባባት እንዳለበት የሚነገረው ኦነግ በፓርቲው ውስጥ ለተረፈጠረው ችግር ገዢውን ፓርቲ ብልጽናን እየወቀሰም ይገኛል፡፡ ይህንኑ በሚመለከት ቃል አቀባዩ "ኦነግ የገጠመው ውስጣዊ መፈረካከስ በብልጽግና ፓርቲ ጣልቃ ገብነት የተፈጸመ ነው" ማለታቸው ተመልክቷል፡፡ ጨምረውም "ብልፅግና የራሱን ከፍተኛ አባላት ከማዕከላዊ አባልነት ሲያግድ ሁሉም በጸጋ ነው የተቀበለው፣ እኛ ግን በፓርቲያችን ውስጥ ያንን ውሳኔ ስንሰጥ ማንም ሊያከብርልን አልቻለም" ሲሉም ቅሬታቸው አሰምተዋል፡፡

ኦነግ በአዲስ አበባ ጦር ኃይሎች የሚገኘው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሜቲ ጽሕፈት ቤቱ በፖሊስ መጠበቅ ከጀመረ ስድስት ወራት እንዳለፈው የሚናገሩት አቶ በቴ፣ "በዚህ ሁኔታ ሥራችንን መሥራት አንችልም በአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የፖርቲው ኃላፊዎችና አባላት እየታሰሩ የምናስመዘግበው እጩ የለንም" ቢሉም ይህ ግን ምርጫውን አንሳተፍም ማለታቸው እንዳልሆነ አንስተዋል፡፡

t.me/geradomedia