🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'የአባሎቼ ሕይወት አደጋ ላይ ቢወድቅ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል' - ኦፌኮ የኦሮሞ ፌዴራላዊ | ገራዶ ሚዲያ

"የአባሎቼ ሕይወት አደጋ ላይ ቢወድቅ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" - ኦፌኮ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ አባሎቹ በአሁን ጊዜ የረሃብ አድማው ከረሃብ አድማ በላይ አልፎ የመታመም ደረጃ ላይ ያደረሳቸውና ሕይወታቸውም አስጊ ሁኔታ ላይ እንድወድቅ ስላደረገ መንግሥት አስቸኳይ የሕይወት ማዳን ሥራ ሠርቶ ግዴታውን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡

ፓርቲው እነዚህ አባላት ተገቢ የሕክምና ዕርዳታ ሳያገኙ ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቅ ከሆነ መንግሥት በሕግም ሆነ በታሪክ ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስቧል፡፡

ኦፌኮ በመግለጫው ጨምሮም "መንግሥት በፈጠራ ክስ ያሠራቸውን አባሎቻችንና ወገኖቻችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አጥብቀን እንጠይቃለን" ያለ ሲሆን፣ "መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ፣ መላው የዓለም ኅብረተሰብ፣ በአገራችን ሕዝቦች ላይ እያንጃበበ ያለው እልቂት እንዲወገድ በተለያዩ ስልቶች መንግሥት ላይ አስፈላጊውን ጫና በማድረግ እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃዎችን እንዲያስቆሙ" ጠይቋል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አባሎች የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም የረሃብ አድማ ማድረግ ጀምረዋል ከተባለ አስራ ሁለት ቀናት ማለፉ የሚታወቅ ነው፡፡

t.me/geradomedia