Get Mystery Box with random crypto!

#ከመግለጫው_የተወሰደ - ሀገራችን ያሉባት ችግሮች ምንም ያህል እንደ ምድር አሸዋ ቢበዙ ፈጽሞ ከ | ገራዶ ሚዲያ

#ከመግለጫው_የተወሰደ

- ሀገራችን ያሉባት ችግሮች ምንም ያህል እንደ ምድር አሸዋ ቢበዙ ፈጽሞ ከዜጎቿ አቅም በላይ እንደማይሆኑ ጽኑ እምነት አለን። የሚፈቱትም ተነጣጥለን ሳይሆን በአንድነትና በትብብር እንደሆነ ገና ከጅምሩ አሳውቀናል።

- የጠላቶቻችን ፍላጎት በጉዞአችን መሐል ወድቀን ግባችንን ሳናሳካ እንድንቀር ነው። በጋራ ቆመን ያጸናነው ቤታችን ፈራርሶ ወደ ትቢያነት ሲቀየር ማየት እንደሚሹ በመግለጽ እኛ ደግሞ ለዚያ የተመቸን ሆነንላቸዋል።

- የትኛውንም ዓይነት ጫና ተቋቁመን፤ የውስጥና የውጭ ፈተናዎቻችንን አልፈን የህዳሴውን ግድብ እንሞላዋለን።

- የወገኖቻችን አሲቃቂ ግድያ፣ ማፈናቀል፣ ቤትና ንብረት ማውደም፣ ነውጥና ሸፍጥ ሁሉ በሀገር ውስጥ ብቻ የተመረተ አይደለም።

- የገጠሙን ችግሮች እንኳን እርስ በእርስ እየተጓተትን ቀርቶ አንድ ሆነንም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ድምጥማጣቸው የሚጠፋ አይደለም።

- መጀመሪያ በውስጣችን ያሉትን ባለ ሁለት ቢላዋዎች እናጸዳለን። ቀን ቀን ለኢትዮጵያ የሚሠሩ የሚመስሉ፤ ሌሊት ሌሊት በኢትዮጵያ ላይ የሚዶልቱ አሉ። እነርሱ ከውጭ ጠላቶቻችን በላይ ዋነኞቹ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡

- የሚደረጉ ማናቸውም የፖለቲካና የመብት እንቅስቃሴዎች ይደገፋሉ። የትግላችን ውጤቶች ናቸውና፡፡ እነዚህ የመብትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ግን ኢትዮጵያን እንዲያናውጡ አንፈቅድም።

- ፖለቲካዊ ጨዋታውን ከጨዋታ ሜዳ ውጭ ለማድረግ ለሚፈልጉት ኃይሎች፣ ትእግሥታችን ማለቁን በዚሁ አጋጣሚ ልንነግራቸው አንፈልጋለን።

- አጥር ላይ ተቀምጠው፣ አሸናፊውን አይተው፣ ከተመቻቸው ሊገቡ፣ ካልተቻቸው ሊሸሹ የሚያስቡ መኖራቸውን አውቀናል። ወቅቱ የምርጫ ነውና መምረጥ አለብን። ወይ እነርሱን እናጸዳለን ወይ ኢትዮጵያን አሳልፈን እንሰጣለን። የኛ ምርጫ ኢትዮጵያን ለእነርሱ ስንል መሠዋት ሳይሆን፤ እነርሱን ለኢትዮጵያ ስንል መሠዋት ነው።

- ኢትዮጵያ ማሸነፏ ላይቀር እንዳታሸንፍ ሲታገሉ የኖሩትን ትታዘባቸዋለች፤ በታሪክ ሂደትም ትቀጣቸዋለች። እርሷ ግን ወጥመዱን በጣጥሳ፣ ሰንኮፉን ነቃቅላ፣ አዚሙን አስወግዳ ያሰበችበት ትደርሳለች።

- ቆም ብለን እናስብ፤ ከሁሉም በፊት ኢትዮጵያን እናስቀድም።

t.me/geradomedia