🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'ኢትዮጵያን በቀጥታ ሳይሆን በውክልና ጦርነት ነው የምንወጋት' ሼሪፍ ኤልሳሊይ ይባላል፤ ግብፃዊ | ገራዶ ሚዲያ

"ኢትዮጵያን በቀጥታ ሳይሆን በውክልና ጦርነት ነው የምንወጋት"

ሼሪፍ ኤልሳሊይ ይባላል፤ ግብፃዊ ነው። የፕሬዚዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ አክቲቪስት ነው። ተከታዩን መልዕክት በቪድዮ ለቋል።

"ኢትዮጵያን ፊትለፊት ጦርነት አንግጥምም። የምንዋጋት በውክልና ጦርነት ነው። በሁሉም ክልሎች የሚደረጉ የሽምቅ ጦርነቶች ላይ የግብፅ ድጋፍ የለበትም ማን አላችሁ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ክልሎች ያሉ የሽምቅ ተዋጊዎች የግብፅ መንግስት ድጋፍ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። መንግስታችንም ይሄንን ብሎ ተቀብሎ ወደስራ ገብቷል።

እኛም የሚያዋጣንን ጠንቅቀን እናውቃለን! አሁን ኢትዮጵያን የሚገዛው ማዕከላዊ መንግስቱ ተዳክሟል። በዚህ በተዳከመ መንግስት ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ከኢትዩጵያ መንግስት ጋር የሚዋጉ ሀይሎች የግብፅ ስትራቴጂካዊ ወዳጅ ናቸው!

ግድቡን ከግብፅ የሄደ ጦር ከሚያፈርሰው ይልቅ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሀይሎች ቢያፈርሱት ነው ለግብጽ አዋጩ መንገድ። እዚህ ጉዳይ ላይ መንግስታችን ተግቶ እየሰራበት ነው። የግብፅ ህዝብ ሆይ .....የግብፅ መንግስት በህዳሴው ግድብ ላይ ለምን እርምጃ አልወሰደም? ይህ ቀይ መስመር ነው ብሎ የለም እንዴ? አትበሉ! መሰራት ያለበንት እየሰራ ነው። ሁሉንም ነገር ለእናተ ማሳወቅ የለበትም!"

የለቀቀውን ቪድዮ ሙሉ ትርጉም በቀጣዩ ሊንክ ታገኛላችሁ።



ውድ ኢትዮጵያዊያን አንድ እንሁን! ጠላቶቻችን እየተሳለቁብን ነው!

Via ሱሌማን አብደላ

t.me/geradomedia