🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

186,240 ገጀራ ተያዘ! በአስመጭ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራ | ገራዶ ሚዲያ

186,240 ገጀራ ተያዘ!

በአስመጭ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186,240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይኔሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ እቃው በዲ/ዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7.7ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ እቃው ከተለቀቀ በኃላ በኢንተለጀስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅ/ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ክትትል የእቃው ባለቤት አዲስ አበባ ዉስጥ ተይዞ ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል።

[ሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ]

t.me/geradomedia