🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የአለም የፕረስ ነፃነት ቀን የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን “መረጃ ለህዝብ ጥቅም” በሚል መሪ ቃል በ | ገራዶ ሚዲያ

የአለም የፕረስ ነፃነት ቀን

የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን “መረጃ ለህዝብ ጥቅም” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በመላው ዓለም እየተከበረ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ በፕረስ ነፃነት ዘንድሮ ከ180 ሀገራት በ101ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን አስታውቋል። ከአምናው በ 2 ደረጃ ዝቅ ብላለች።

ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ቡድን ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሰረት ኖርዌይ ጥሩ የፕሬስ ነጻነት አላት ተብላ በአንደኝነት ደረጃ ተቀምጣለች። ለፕሬስ ነጻነት ከማይመቹ ሀገራት ውስጥ ደግሞ ቻይና 177ኛ ደረጃ ስትይዝ ቱርክሜንስታን 178ኛ፣ ሰሜን ኮሪያ 179ኛ እና ኤርትራ 180ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የሚዲያ ተቋማትና ግለሰቦች እውነትን ብቻ ደግፈው ህዝብን ሊያገለግሉ ይገባል። መንግስትም ከእነዚህ፤ እውነትን ብቻ ደግፈው ህዝብን እያገለገሉ ካሉ የሚዲያ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ እጁን ሊሰበስብና የፕረስ ነፃነትን ማክበር አለበት።

#PressFreedom

t.me/geradomedia