🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የጌታችን ምጽአት ፅሑፉን እስከ መጨረሻው አንብቡት ማቴዎስ 24 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ | GOD'S GOSPEL

የጌታችን ምጽአት

ፅሑፉን እስከ መጨረሻው አንብቡት

ማቴዎስ 24 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ “በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤
³¹ መላእክቱንም ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱም ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ።
³² “ከበለስ ዛፍ ይህን ትምህርት ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ።
³³ እንደዚሁም እነዚህን ሁሉ ስታዩ፣ እርሱ በደጅ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።
³⁴ እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
³⁵ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።


የበለሱ ዛፍ ምሳሌ ትርጉም ምን ማለት ይሆን??

ኢየሱስ ስለሚመጣበት ወቅት #ፍንጭን ሰጥቶናል።
የበለሷ ዛፍ:
1.ስትለመልም
2.ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣
-ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ።

ኢየሱስ የበለስ ዛፏን እንደምትለመልምና ቅጠል መሰብሰብ #ከጀመረች_አንስቶ
1.የኢየሱስን ዳግም ምፅአት፣
2.የእውነተኛ ክርስቲያኖች መነጠቅ፣
3.የሃሰተኛው ክርስቶስ መነሳትና
4.በሰው ልጅ ታሪክ ዓለም ታይቶ የማይታወቀውን መከራ እንደሚሆን ድረስ አንድ ትውልድ(100 ዓመታት) #እንደማያልፍ_በግልፅ ነግሮናል።

"ይህ ሁሉ (ከላይ የተጠቀሱት) እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ #አያልፍም።"ብሎ ተናግሯል።

እግዚአብሔር በኢዩኤል 6:7 ላይ የበለስ ዛፉ #የእርሱ ምድር ፣ #እስራኤል እንደሆነች #በግልፅ ይናገራል። በታሪክ እንደምንረዳው #በ70 AD ላይ እስራኤል ሃገር ተበታትና አይሁዶች በየሃገሩ እንደስደተኛ እንደኖሩ እናውቃለን። ለ2000 አመታት እስራኤላውያን ከምድራቸው ተባረው በተለያየ ሃገር ሲኖሩ ቆይተዋል። ነገር ግን #በ1948 ከሁለት ሺህ አመታት በኋላ በመሰባሰብ በቀድሞ ምድራቸው ላይ የሰፈሩ የአረብ ነዋሪ ፍልስጥኤማውያንን በመዋጋት እስራኤል እንደገና ሃገር መሆን ችላለች። ይህች ታናሽ ሃገር የመፅሃፍ ቅዱሳችን #መሃከለኛ ታሪክ እንደሆነች የታወቀ ነው። የምናነበው መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ከእስራኤላውያን ጋር የነበረው ግንኙነት የሚያሳይ ነው። ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ለእነርሱ ነበር። "ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም ነገር ግን ለተቀበሉት ሁሉ በስም ለሚያምኑ (እኛ አህዛቦች) የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው" ዮሐንስ 1:12።
ስለዚህ የመጨረሻውን ዘመን እንድናውቅ ራሱ ኢየሱስ ከሰጠን ማስጠንቀቂያና ማንቂያ ደውሎች አንዱ የሆነው ክስተት #ለሁለት_ሺህ አመታት ከዓለም ካርታ ጠፍታ የነበረችው #እስራኤል_ወደ_ካርታ_መመለሷ ነው።

እስራኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ #በ1948 ጦርነት በዙሪያዋ ያሉ የአረብ ሃገራትን እስካሁን ድረስ በታሪክም እንደተማርነው #ተዓምራት በሚመስል መንገድ ለብቻዋ 6 አረብ ሃገራትን ድል ነስታ የጥንት ጊዜ ምድሯን ተቆጣጠረች። ይህ ከሆነ በኋላ አይሁዶች በራሳቸው ዕብራይስጥ ቋንቋ "አሊያህ" ብለው በሚጠሩት የአይሁዶች ወደ ሃገራቸው መመለስ (ሁለተኛው ዘፀዓት) በ1948 ጀመረ። እስራኤላውያን ሁሉ ከዓለም ጫፍ እስከጫፍ እንደስደተኛ ከተቆጠሩበት ምድር ወደ እናት ሃገራቸው መመለስ ጀመሩ። ሃገራቸውንም ለማመን በሚከብድ ፍጥነት ማልማት ጀመሩ። ዛሬ ላይ ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሃገራት መካከል እስራኤል አንዷ ናት። በእኛም ሃገር በኢትዮጵያ ለብዙ መቶ አመታት ፣ የእጅ ባለሞያተኛ በመሆናቸው ብቻ አይሁዶች እየተጠሉ እንደኖሩ እናውቃለን ፣ በጎንደር አካባቢ እንደኖሩ እስካሁንም ያልሄዱ ጥቂት አይሁዶች እንደሚኖሩ እናውቃለን(ፈላሻዎች)። #የአይሁች_ወደ_እስራኤል_መመለስ_እና_የእስራኤል_ምድር_ማቆጥቆጥ ፣ #ማደግና #በፍጥነት_መበልፀግ_ወደ_በለስ_ዛፍ_ቅጠሎች_መመለስን_ያሳያል።
እጅግ ለማመን በሚያስቸግር መንገድ እስራኤል በ21ኛው ክፍለ ዘመን የቴክኖሎጂን ኢንደስትሪ #በቅድሚያ የምትመራ ብቸኛ ሃገር #እስራኤል ናት። በህክምና፣ በግብርና ፣ በአዳዲስ ፈጠራ፣ በመከላከያ ጦር፣ በትምህርት #ከቀዳሚ ሃገሮች የምትጠቀስ ሃገር ናት። #ይህ_ሁሉ_የበለሷን_ዛፍ_መለምለም_ያሳያል።

ኢየሱስ ዳግመኛ መምጣትና የእውነተኛ ክርስቲያኖች ንጥቀት፣ የሃሰተኛው ክርስቶስ መነሳት የበለስ ዛፏ ማቆጥቆጥ ከጀመረች አንስቶ አንድ ትውልድ(100 አመት) #እንደማያልፍ በግልፅ ተናግሯል።


በታሪክ ውስጥ የትኛውም ትውልድ የበለስ ዛፏን ማቆጥቆጥ #ያየ_የለም።
እኛ ግን በአይናችን ይሄ ሁሉ ትንቢት ሲፈፀም እያየን ነው።

ከምንግዜው በላይ ልንነቃና በእያንዳንዱ ቀናችን እግዚአብሔርን በመፍራትና በመታዘዝ፣ ራሳችንን ከክፉ በማራቅ፣ የክርስቶስን ወንጌል እየተናገርን ብዙዎችን ከሲዖል የምንናጠቅበት ያለቀ ሰዓት ላይ እንጂ ወደኋላ ተመልሰን ከሃጢአት ጋር የምንጫወትበት ጊዜ ላይ አይደለንም።

ይሁ ሁሉ ሲሆን መዳናችሁ ከትላንት ይልቅ እንደቀረበ #እወቁ ያለው ጌታ እንድናስተውልና ንስሃ ገብተን ፣ ከጌታ ጋር ያለን ግንኙነት የምናድስበት፣ ራሳችንን በቃል፣ በፀሎት በቀረችንም #ጥቂት ጊዜ ብትሆን ለጌታ የምንሮጥበት ጊዜ እንጂ ራሳችንን የምናስቀድምበት ጊዜ ላይ አይደለንም።

ልብ ያለው ያስተውል!
ኢየሱስ ሊመጣ በደጅ ነው፣ ቤተክርስቲያን ግን ከባድ እንቅልፍ ላይ ናት። ራሳችሁን አንፁ፣ አስተካክሉ፣ አዘጋጁ።

ኢየሱስ ይመጣል!
አሜን!

#የፓስተር_በቀለ_ወልደ_ኪዳን
"ከሌሊቱ ስንት ሰዓት ነው?" የሚለውን መፅሃፍ እንድታነቡ አበረታታችኋሁ።

በተጨማሪም ይህን video አሁኑኑ ተመልከቱ