🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የቀጠለ...#3 እስራኤል እንደ ሀገር 73ኛ ዓመታቸውን አክብረዋል። ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ | GOD'S GOSPEL

የቀጠለ...#3

እስራኤል እንደ ሀገር 73ኛ ዓመታቸውን አክብረዋል።

ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ #ትውልድ አያልፍም (ማቴ 24፡34፣ መዝሙረ ዳዊት 102፡18፣ ሆሴዕ 6፡2)
*ትውልድ*=100 አመት
ይህ 100 ዓመት የጀመረው #እስራኤል ሀገር ስትሆን እ.ኤ.አ. በ1948 ነው።

ስለዚህም 1948+100አመት=2048 ዓ.ም

2048-2021=27ዓመታት። እና
27ዓመት -7 ዓመት የመከራ ዓመታት =20 ዓመት።

ስለዚህ አሁን እስከ ንጥቀት 20 ዓመታት ድረስ ብቻ አለን።( ይህ እውነት ነው..እመኑ።)
የቤተ ክርስቲያን ዘመን እየቀረበ ነው። በጣም ከምታስቡት በላይ #ባለቁ_ሰዓታት ውስጥ ነው ያለነው።

#ከመቼውም ጊዜ በላይ #ወንጌል_መሰበክ ያለበት ጊዜ ነው። መልዕክቱ ግልጽ ነው ጆሮ ያለው ይስማ።

ለክፋት ጊዜ የለም
ለቅናት ጊዜ የለም
ለጥላቻ ጊዜ የለም
ለዘረኝነት ጊዜ የለም
ለራስ ወዳድነት ጊዜ የለም

አሁንም #በእውነትና_በእምነት ውስጥ እንዳላችሁ ራሳችሁን መርምሩ። ንስሐ ግቡና ወደ መጀመሪያው ፍቅራችሁ ተመለሱ...ተጽዕኖአችሁን #ለወንጌል ተጠቀሙበት።ወደኋላ አትበሉ።ጊዜው እጅግ በጣም አጭር ነው።የሰማችሁትና ያመናችሁት ኢየሱስ #ከምትገምቱት በላይ #ፈጥኖ_ይመጣል።

በቀን ለአንድ ስው #ወንጌልን ለመስበክ ጥረት አድርጉ። ይህን ማድረግ ከቻልን:-
1×30=30 ነፍሳት በወር
30×12 ወር =3,600 ነፍሳት በዓመት
3600×20= 72,000 ነፍሳት በ 20 ዓመት


“ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ #ዘመኑን_እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ #ቀርቦአልና።”
—ሮሜ 13፥11

Join and share it
@godsgospel
@godsgospel